ፊፋና የአውሮፓ እግር ኳስ በእግር ኳስ ውድድሮች በሚያጋጥሙ የዘረኝነት ተግባራት ላይ ጥፋት የሰሩ ተጨዋቾችና የክለብ ደጋፊዎችን በማያዳግም ቅጣት አለማስተማራቸው ችግሩ እንደካንሰር ስፖርቱን ተጠናውቶ ሊገለው ይችላል የሚሉ ስጋቶችም በዝተዋል፡፡የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ባለው የንግድ እንቅስቃሴና ከመላው ዓለም የመጡ ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች እንደመብዛታቸው በእግር ኳስ ስፖርት እያጋጠመ ያለውን ዘረኝነት ተጎጂ ያደርገዋል፡፡ በሊጉ የሚደረጉ ጨዋታዎች በቀጥታ የቴሌቭዠን ስርጭት ሲተላለፉ መላው የሰው ልጅ ስለሚታደማቸው ተጨዋቾች በሜዳ ላይ በሚያሳዩት ባህርይ ምን ያህሉን የዓለም ህዝብ ስሜት ሊጎዱ እንደሚችሉ መገንዘብ አለማቻላቸውን የሚወቅሱ ሚዲያዎች ጥቂት አይደሉም፡፡ዘረኝነት፣ አለመቻቻልና ማግለል በእግር ኳስ በሜዳ ውስጥና ከሜዳ ውጭ አሉታዊ ተጽእኖ በመፍጠር መቀጠላቸው ያሳስባል፡፡ ላለፉት 10 ዓመታት ፉትቦል አጌንስት