Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 19 November 2011 15:16

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ቀጣይ ትኩረት ያስፈልገዋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ብራዚል በ2014 ለምታስተናግደው 20ኛው ዓለም ዋንጫ ለማለፍ በአፍሪካ ዞን የሚደረገውን የምድብ ማጣርያ ሰሞኑን ለመቀላቀል የበቃው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ቀጣይ ትኩረት ያስፈልገዋል፡፡
ብሄራዊ ቡድኑ በ20ኛው የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣርያው የዛሬ ሳምንት ጅቡቲ ላይ ከሶማሊያ ያደረገውን ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ሲመለስ በርካታ ደጋፊዎቹን አበሳጭቶ የነበረ ሲሆን በሳምንቱ አጋማሽ ላይ በመልስ ጨዋታው 5ለ0 አሸንፎ ወደ ምድብ ማጣርያው መግባቱ የተፈጠረውን ተስፋ መቁረጥ አብርዶታል፡፡

ዋልያዎቹ ሶማሊያን በፍፁም የጨዋታ ብልጫ 5ለ0 ሲያሸንፉ ከ5 በላይ የግብ እድሎችን አምክነው ሲሆን ጎሎቹን የመጀመርያውን የመከላከያው ኡመድ ኡክሪ እንዲሁም እያንዳንዳቸው ሁለት ጎሎችን የቅዱስ ጊዮርጊሱ ሽመልስ በቀለ እና የደደቢቱ ጌታነህ ከበደ አስቆጥረዋል፡፡ ለ20ኛው ዓለም ዋንጫ የምድብ ማጣርያ ኢትዮጵያ በምድብ 1 ከደቡብ አፍሪካ፤ ከቦትስዋና እና ከመካከለኛው አፍሪካ ጋር የተደለደለች ሲሆን በግንቦት ወር መጨረሻ ከሜዳዋ ውጭ በጆሃንስበርግ ከደቡብ አፍሪካ ጋር በምታደርገው የመጀመርያ ጨዋታ ፉክከሯን ትጀምራለች፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ አፍሪካ ለሚደረገው የ2013 የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከቤኒን ጋር የተመደበ ሲሆን የደርሶ መልስ ጨዋታውን በሜዳው እንደሚጀምር ታውቋል፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ከበቃ 30 ዓመታት ያለፈው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቀጣይ ለአፍሪካ ዋንጫ እና ለዓለም ዋንጫ በሚያደርጋቸው የማጣርያ ጨዋታዎች ውጤታማ እንዲሆን የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተገቢው ትኩረት ያስፈልገዋል፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ በእነዚህ የማጣርያ ውድድሮች በቂ የዝግጅት ጊዜ በመመደብ፤ በዛ ያሉ የአቋም መፈተሻ ግጥሚያዎችን በማድረግ እና በተጠናከረ የፋይናንስ አቅም መስራት እንዳለበት ይመከራል፡፡

Read 3231 times