ሰሞኑን በመላው ዓለም በጠቅላላ 283.5 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንዳስገኘ ታውቋል፡፡ በ110 ሚሊዮን ዶላር በጀት በ”ሰሚት ኢንተርቴይመንት” የተሰራው የዚህ ፊልም ሁለተኛ ክፍል ከዓመት በኋላ ለተመልካች ይቀርባል፡፡ በስቴፌን ሜየር የቫምፓየር መፅሃፍ ላይ ተመስርተው የተሰሩት የመጀመርያ ሶስት ክፍል ፊልሞች በዓለም ዙርያ 1.8 ቢሊዮን ዶላር አስገብተዋል፡፡ የ”ትዋይላይት” ገበያ በአራት ፊልሞችና ሶስት ተከታታይ መፅሃፎች ሽያጭ ብቻ አያበቃም፡፡ ከፊልሙ ጋር የተያያዙ የአልባሳት፤ የተለያዩ ቁሳቁሶችና ምርቶች ገበያም ደርቷል፡፡ የፊልሙ መሪ ተዋናዮች ሮበርት ፓቲርሰንና ክርስትያን ስተዋርት በመጨረሻዎቹ ሁለት ፊልሞች እያንዳንዳቸው 25 ሚሊዮን ዶላር ተከፍሏቸዋል፡፡ የመፅሃፍቱ ደራሲ ስቴፈን ማዬር ደግሞ ባለፈው ዓመት ገቢዋ 40 ሚሊዮን ዶላር መድረሱን ያመለከተው ፎርብስ መፅሄት፣ ሶስቱ የ”ትዋይላይት” መፅሃፍት በዓለም ዙርያ ሽያጫቸው ከ100 ሚሊዮን ዶላር መብለጡን ዘግቧል፡፡