Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 26 November 2011 08:48

ጂሚ ሄንድሪክስ የምንጊዜም ምርጥ ጊታሪስት ተባለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ጂሚ ሄንድሪክስ በሮክ ኤንድ ሮል ሙዚቃ ታሪክ የምንጊዜም ምርጥ ጊታሪስት ሆኖ መመረጡን “ሮሊንግስቶን” መፅሄት አስታወቀ፡፡ ጊታሩን በፈለገው ሁኔታ በመጫወት የሚታወቀው ጂሚ ሄንድሪክስ፤ “ዘ ፐርፕል ሄዝ” እና “ዘ ስታር ስፖንጅ ባነር” በተባሉ ሁለት አልበሞቹ በስቱድዮም ሆነ በመድረክ አስደናቂ የጊታር አጫዋወት ማሳየቱን ባለሙያዎች መስክረዋል፡፡ ከ31 ዓመት በፊት በ27 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ጂሚ ሄንድሪክስ፤ ከ10 በላይ አልበሞችን አውጥቷል፡፡መፅሄቱ ምርጫውን ያካሄደው ታዋቂ የሙዚቃ ኤክስፕርቶችና አሁን በስራ ላይ ያሉ ምርጥ ጊታሪስቶች ያደረጉትን ግምገማ እና የሰጡትን ድምፅ መሰረት አድርጎ ነው፡፡ በሮክ ኤንድ ሮል ሙዚቃ ታሪክ ጉልህ ሚና ላላቸው 10 ምርጥ ጊታሪስቶች በወጣው ደረጃ መሰረት፤ ኤሪክ ክላፕተን፤ ጂሚ ፔጅስ፤ ኬዝ ሪቻርድስ፤ ጄፍ ቤክ፤ቢቢ ኪንግ፤ ቻክ ቤሪ፤ ኤዲ ቫንሀለን፤ ዱዋኔና ኦልማንና ፒቴ ታውንሼንድ ከ2ኛ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ አግኝተዋል፡፡

Read 2964 times

Latest from