Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 26 November 2011 08:52

የሪሃና ቪድዮ ፈረንሳዊያንን አይመጥንም ተባለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የሪሃና “ሁ ኦውንስ ማይ ኸርትስ› የሙዚቃ ቪድዮ፤ በፈረንሳይ መታገዱን “ዘ ሚረር” ጋዜጣ ዘገበ፡፡ የሙዚቃ ቪድዮው፤ ማን ሊመለከተው እንደሚገባ የሚያሳውቅ ደረጃ አለመያዙና ለፈረንሳዊያን የሚመጥን አለመሆኑ ለእገዳው ምክንያት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በቪድዮው ሪሃና የምታሳየው “መረን የለቀቀ ዳንስ መጥፎ ነው” በሚል ተወግዟል፡፡

በሌላ በኩል በሳምንቱ አጋማሽ ላይ ለገበያ የበቃው የሪሃና “ቶክ ዛት ቶክ” የተሰኘ አዲስ አልበም በፖፕ የሙዚቃ ስልት ስኬታማ ሊያደርጋት እንደሚችል ኒውዮርክ ታይምስ ጠቁሟል፡፡ በአልበሙ ውስጥ የተካተቱት ዘፈኖች በህይወቷ ያጋጠሟትን ቀውሶች የማያንፀባርቁ እንደሆኑ የዘገበው ኒውዮርክ ታይምስ፤ ንፁህ የፈጠራ ችሎታዋን እንዳሳየችበት ገልጿል፡፡ በዴፍ ጃም ሬከርድስ የታተመው የአርቲስቷ 6ኛ አልበም የሆነው “ቶክ ዛት ቶክ” ባለፈው ረቡእ በመላው ዓለም ለገበያ የዋለ ሲሆን ባንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሽያጩ ሩብ ሚሊዮን ኮፒ እንደደረሰ ተገምቷል፡፡ ሆኖም ይሄው የሪሃና አልበም ሰሞኑን ለገበያ ከበቁት ከአምስት በላይ ታዋቂ ሙዚቀኞች አዳዲስ አልበሞች ከባድ ፉክክር እንደገጠመው ታውቋል፡፡ አዳዲስ አልበሞቻቸውን ለገበያ ካበቁት መካከል ሜሪ ጄብሌጅ፤ ማይክል ጃክሰንና ቴይለር ስዊፍት ይገኙበታል፡፡

 

Read 2695 times Last modified on Saturday, 26 November 2011 08:54

Latest from