Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 26 November 2011 08:52

በአሜሪካ የሙዚቃ አዋርድ ሴቶች የበላይነት

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሰሞኑን በተካሄደው 39ኛው የአሜሪካ ሙዚቃ አዋርድ ስነስርዓት ላይ ሴት ድምፃውያን በርካታ ሽልማቶችን በመሰብሰብ ከፍተኛ የበላይነት ተጐናፀፉ፡፡ አሜሪካዊቷ የካንትሪ ሚውዚክ አቀንቃኝ ቴይለር ስዊፍት ሶስት ትልልቅ ሽልማቶችን ያገኘች ሲሆን አርቲስቷ “የዓመቱ ምርጥ አርቲስት” ሽልማትን በመውሰድ ተፎካካሪዎቿን አዴሌን፤ ኬት ፔሪን እና ሌዲ ጋጋን በልጣለች፡፡ በ2011 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) የ45 ሚሊዮን ዶላር ገቢ የተመዘገበላት የ21 ዓመቷ ቴይለር ስዊፍት፤ ከአንድ ዓመት በፊት ያወጣችው “ስፒክ ናው” የተባለው አልበሟ በመላው ዓለም 20 ሚሊዮን አልበምና 34.5 ሚሊዮን ዲጂታል ቅጂዎች ተሸጦላታል፡፡

በሌላ በኩል በአራት የሽልማት ዘርፎች ታጭታ የነበረችው እንግሊዛዊቷ አዴሌ፤ የዓመቱን ከፍተኛ ሽያጭ ባስመዘገበው “21” የተሰኘው አልበሟ፤ በፖፕና ሮክ ስልት “የዓመ+ቱ ምርጥ አርቲስት” እና “የምርጥ አልበም” ሽልማቶችን አግኝታለች፡፡ የበርባዶስ ተወላጇ ኒክ ማንጅ እንዲሁ “ፒንክ” በተባለው አልበሟ በራፕና ሂፕሆፕ ዘርፍ፣ የ”ዓመቱ ምርጥ አርቲስት” እና “ምርጥ አልበም”ን ሽልማቶች ስትወስድ፤ ሪሃና በሶል ኤንድ አር ኤንድ ቢ ዘርፍ የ”ዓመቱ ምርጥ አልበም”፣ ጄኒፈር ሎፔዝ ደግሞ የ”ዓመቱ ምርጥ የላቲን አርቲስት” ተብለው ተሸልመዋል፡፡


 

Read 2355 times Last modified on Saturday, 26 November 2011 08:54