Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 26 November 2011 08:55

አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ በአውስትራሊያ ሚዲያዎች ተደነቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በአውስትራሊያ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ሙዚቃ ኤክስፖ፣ የኢትዮ ጃዝ ፈጣሪው ሙላቱ አስታጥቄ ከፍተኛ ክብር እንደተቀዳጀ በመጥቀስ የተለያዩ የአውስትራሊያ ሚዲያዎች አድንቀውታል፡፡ የ68 ዓመቱ አርቲስት ሙላቱ የመግቢያ ትኬቶቹ ሙሉ ለሙሉ በተሸጠበት የኤክስፖው ኮንሰርት ላይ ከሜልቦርኑ “ብላክ ጂሰስ ኤክስፒሪያንስ” ባንድ ጋር ባለፈው ቅዳሜ ሥራውን አቅርቧል፡፡ ዘጠኝ አባላት ያሉት የሙዚቃ ባንዱና ሙላቱ አስታጥቄ በጋራ መስራት ከጀመሩ ሁለተኛ ዓመታቸውን አስቆጥረዋል፡፡ ሙላቱ በኤክስፖው ላይ ከተጫወታቸው ሙዚቃዎች “የከርሞ ሰው” የተባለው የ”ብሮክን ፍላወርስ” ፊልም ማጀቢያ ሙዚቃ ይገኝበታል፡፡ በሜልቦርን ከተማ በሙዚቃ ኮንሰርቶችና ኮንፍረንሶች የሚካሄደው ኤክስፖ፤ ለአራት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ዘንድሮ የተዘጋጀው ለአራተኛ ጊዜ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በዓለም አቀፉ የሙዚቃ ኤክስፖ ለመሳተፍ ከ600 በላይ የዓለም ሙዚቀኞች አመልክተው እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Read 4318 times Last modified on Saturday, 26 November 2011 08:59