የታምራት ገዛኸኝ ሥዕሎች ዛሬ ይታያሉ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የስፔን ኤምባሲና “UN Women” የሴቶችን ፆታዊ ጥቃት ለመዘከር የፊልም አውደ ርዕይ በጋራ እንዳዘጋጁ ተገለፀ፡፡
በዩኒቨርሲቲው ኤትኖግራፊክ ሙዚየም የሚቀርበው የፊልም አውደርእይ “ከጥቃት ነፃ ለሆነ ሕይወት በአንድነት” የሚል መልእክት ያዘለ ሲሆን ዛሬ በእውቋ ሶማሊያዊት ልእለ ሞዴል ዋሪስ ድሬ ሕይወትን አስመልክቶ የተሰራው “Desert Flowers” ለእይታ ይቀርባል፡፡ሰኞ “Take my Eyes” የተሰኘው የስፔን ፊልም የሚቀርብ ሲሆን ሌሎች ፊልሞችና የፎቶግራፍ አውደርዕይም ተዘጋጅቷል፡፡ የሰዓሊ ታምራት ገዛኸኝ ሥዕሎች ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት ዘነበወርቅ አካባቢ በሚገኘው “ሌላ የሥዕል ጋለሪ” የሚከፈት ሲሆን እስከ ታህሳስ 8 ቀን 2004 ዓ.ም ከረቡዕ እስከ እሁድ ለሕዝብ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡