Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 26 November 2011 09:02

የቅጂና ተዛማጅ መብት የጣሱ ተቀጡ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በቅጂና ተዛማጅ መብቶች በመጣስ የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦች በእስር ተቀጡ፡፡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎትን ጠቅሶ የኢትዮጵያ ኦዲቪዥዋል አሳታሚዎች ማህበር ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ ሰኞ እለት የተሰጠው የፍርድ ቤት ውሳኔ በ116 ሕገወጥ ቅጂ የተከሰሰው በርሄ አስረስ እና በ87 ሕገ ወጥ ቅጂ ሄኖክ ሃይሉ የተባሉ ግለሰቦች በሦስት ዓመት ከሦስት ወር እና በሶስት ዓመት ፅኑ እስራት የተቀጡት ነሃሴ 21,2003 ዓ.ም ክስ ከተመሠረተባቸው በኋላ ነው፡፡

የስፑትኒክ ሙዚቃ ቤት ባለቤት አቶ ፋሲል ሙሉሥራ በጳጉሜ 2002 ዓ.ም ሕገወጥ ቅጂ ማባዣ ማሽን እና ካሴት ተገኝቶባቸው ክስ መመሥረቱ የሚታወቅ ሲሆን እሳቸውም የሁለት አመት ፅኑ እስራት ተወስኖባቸዋል፡፡ የ164 ሕገወጥ ቅጂ የተገኘባቸው ዮሴፍ እሸቱ ሕዳር 6 የሦስት ዓመት ከሰባት ወር ፅኑ እስራትና ለሁለት ዓመት ከሕዝባዊ መብት እንዲገደቡ መቀጫ ተጥሎባቸዋል፡፡ ነሀሴ 21,2003 ዓ.ም በተደረገ ዘመቻ ከተያዙ 250 የሕገወጥ ቅጂ ተጠርጣሪዎች መካከል 143ቱ በአዲስ አበባ መያዛቸው ይታወቃል፡፡

 

Read 2257 times Last modified on Saturday, 26 November 2011 09:04

Latest from