ሁለት ሩስያውያን ፎቶ አንሺዎች የፎቶግራፍ ሥራዎቻቸውን በአዲስ አበባ አቀረቡ፡፡ በፑሽኪን አዳራሽ ባለፈው ረቡዕ የተከፈተው የሩስያውያኑ ፎቶግራፍ አውደርእይ ለአስር ቀናት የሚቆይ ሲሆን የሞስኮን የአሁን ገፅታ፣ የሩስያ ብሔራዊ ፓርኮችን የሚያሳዩ እና የተለያዩ ሕዝቦችን ፈገግታ የሚያሳዩ 150 ፎቶግራፎች ቀርበውበታል፡፡ ዶር.ቫሲሊ ክሊሞቭ እና ቦሪስ ቫርሸኒን የተባሉት እነዚሁ ሩስያውያን አፍሪካ አህጉር ላይ በጋራ አውደርእይ ሲያቀርቡ የመጀመርያቸው ሲሆን በኢትዮጵያ ለአንድ ወር በመቆየት ተዘዋውረው ፎቶግራፍ እንደሚያነሱ እና በማዕከሉ ጋባዥነት ወደ ኢትዮጵያ እንደመጡ ማወቅ ተችሏል፡፡