Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 26 November 2011 09:21

የግጥም ጥግ

Written by 
Rate this item
(32 votes)

ሻማ ሆይ
ሻማ ሆይ ብሪ! ብሪ!
በጸዳልሽ ታመኝ፤ ኩሪ፡፡
ለጸዳልሽ ጸዳል ሰጥተሽ፤
የቀን ጽልመቴን አውግጊ፡፡
ድብት መንፈሴን አፍግጊ፡፡
“አይዞክ!፣ ግድ የለም!” በይኝ፤
“ትንሣኤ ሙታንን” እያጣቀስሽ፤
“የሟችን ነፍስ ይማር!” እያልሽ፡፡
ሻማ ሆይ ተንተግተጊ
ለእኔ ብለሽ ትጊ፤ ፍጊ፡፡
የነዲድሽ ልሳን ይርዘም፡፡
ውጥኔ ሕብሩም ይድመቅ፡፡
የውዕየትሽ ሞገድ ይትመም፡፡
ብሩህ መዓልት ውስጥ ይለቀቅ፡፡
ሡራኄሽ በልቡናዬ ተገልጾ፣
የጽልመት ድባቤን ይግፈፍ፡፡
ስኂኖትሽ በውስጤ ኅዋ ሠርጾ፣
የዝክሬን በረድ ይቅረፍ፡፡
ሻማ ሆይ ተንቦግቦጊ፡፡
በእሳተ-ላንቃሽ ተመንደጊ፡፡
የውስጤን በረድ ያቀልጥ ዘንድ፤
ውዕየትሽ ወዓይያንን ይብለጥ፡፡
የትካዝ ባሕሬን ያትንን፤
የሐዘን እዤን ይምጠጥ፡፡
ሻማ ሆይ ፍኪ፣ ፍጊ እንጂ፤
ምነው ጥርዥ-ብርዥ አልሽሳ!
ነድደሽ ማለቅሽ ነውሳ!
ንዴት ለአንቺ ብቻ አይደል፤ ለወንድሜም አላዋጣ፡፡
በቶሎ ማለፍ፣ መክሰም ነው፤ የብሩሆች ኹል ዕጣ፡፡
ግ.ጌ
ኦክስፎርድ
ለታናሼ ሙት-ዓመት ማዘከሪያ ተጻፈ
ግንቦት 9 1997 ዓ.ም

Read 11657 times

Latest from