Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 03 December 2011 08:35

ሜሪል ስትሪፕና ብራድ ፒት የአመቱ ምርት ተባሉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሜሪል ስትሪፕና ብራድ ፒት በኒውዮርክ ፊልም ሃያሲያን የአመቱ ምርጥ ተዋናዮች መባላቸውን ኒውርክ ታይምስ ዘገበ፡፡ 84ኛው የኦስካር ሽልማት ስነስርዓት ሊካሄድ ሶስት ወራት ቢቀሩም የአመቱን ታላላቅ የስኬት ክብሮች እነማን ይወስዳሉ የሚለው ጉዳይ በስፋት እያነጋገረ ነው፡ በኒውዮርክ የሚሰሩና ከተመሰረተ 80 አመት የሆነውን ኒውዮርክ ፊልም ክሪትክስ ሰርክል የተባለ ቡድንን የሚወክሉ 33 የፊልም ሃያሲዎች ሰሞኑን ይፋ ባደረጉት መረጃ የአመቱ ምርት የፊልም ስራዎችንና ባለሙያዎችን መርተዋል፡፡

በሃያሲያኑ ግምገማ መሰረት በቅርቡ ለእይታ በሚበቃው” ዘ አይረን ሌዲ” በተባለ ፊልም የቀድሞዋን የእንግሊዝ ተቅላይ ሚኒስትር ማርጋሬት ታቸር የተወነችው ሜሪል ስትሪፕ የአመቱ ጎበዝ ተዋናይት ሲሏት “መኒ ቦል” እና “ትሪ ኦፍ ላይፍ” በተባሉ ሁለት ፊልሞች ድንቅ ትወና ያሳየውን ብራድ ፒት ጎበዝ ተዋናይ አድርገውታል፡፡ “ዘ አርቲስት” የተሰ’ውን ፊልም የአመቱ ምርት ፊልም ብለው የመረቱት ሃያሲያኑ ፊልሙን የሰራውን ማይክል ሃዛናቪከስ የአመቱ ምርት ዲያሬክተር ነው ብለዋል፡፡
በኒውዮርክ ከተማ የሚሰሩት ሃያሳውያኑ የአመቱ ምርት ብለው የመለመሏቸውን የፊልም ምርት ስራዎችና ባለሙያዎች ያሳወቁት በሆሊውድ የአዋርድ ስነስርአቶች የሚካሄድባቸው ወቅቶች ሲቃረቡ ተፅእኖ ለማሳደር ነው፡፡ሜሪል ስትሪፕ በ30 አመታት የትወና ዘመኗ በምርት ተዋናይነት ለኦስካር 16 ጊዜ ታችታ 2ቱን የወሰደች ሲሆን ዘንድሮ ለ17 ጊዜ እቹ ሆና በመቅረብ 3 ክብሯን የማግ’ት ግምቱ አጋድሎላታል፡፡ የ62 አመቷ ሜሪል ስትሪፕ የኦስካር ክብርን መውሰድ ዛሬም ቢሆን ያጓጓል ብላለች፡፡ ሜሪል ስትሪፕ መሪ ተዋናይ የሆነችበት “ዘ አይረን ሌዲ” 2012 ከገባ በመጀመርያው ሳምንት ለእይታ ይበቃል፡፡ የማርጋሬት ታቸር ቤተሰብ አንዳንድ አባላትና የፖለቲካ አጋሮቻቸው በፊልሙ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ከልክ ያለፈ ስሜታዊ ተደርገው ተስለዋል በሚል ተቃውሞቸውን ገልፀዋል፡፡

 

Read 2039 times Last modified on Saturday, 03 December 2011 08:36