Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 03 December 2011 08:37

ፈቲያ በ”ሚስ ቱሪዝም ኪውን ኦፍ ዘይር” ላይ ተሳተፈች

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከ2 ሳምንት በፊት በቻይናዋ ከተማ በተደረገው ሚስ ቱሪዝም ኪውን ኦፍ ዘይር ውድድር ላይ ፈቲያ መሃመድ ኢትዮጵያን ወክላ ተሳተፈች፡፡ ኡጋንዳ፣ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ ሌሎች ከአፍሪካ የተወከሉ ተወዳዳሪዎች ናቸው፡፡ ፈቲያ ወደ ቻይና ያደረገችው ጉዞ በማሳካት ሴንትራል ጤና ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅና በላይአብ ኢንተርፕራይዝ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በውድድሩ ላይ ከአለም ዙርያ 53 አገራትን የወከሉ ቆነጃጅት ተሳትፈው የውበት አክሊሉን የተቀዳጀችው ህንድን የወከለችው ናት፡፡ 17ኛው ሚስ ቱሪዝም ኪውን ኦፍ ዘ ይር በቻይና የጂንክሳይ ክልል ዋና ከተማ ይንግታን የተደረገ ሲሆን አላማው የአገራትን ወዳጅነት ለማጐልበት፤ የባህልና የልምድ ልውውጥ ለማድረግና ቱሪዝምን ለማስፋፋት በሚል ነው፡፡ ሚስ ዩክሬን፤ ሚስ ፖላንድ፤ ሚስ ማሌዝያና ሚስ ኮርያ እስከ አራተኛ’ ያለውን ደረጃ አከታትለው ወስደዋል፡፡

 

Read 3412 times Last modified on Saturday, 03 December 2011 08:39