ሰኞ ምሽት በ12 ሰዓት የኒውዚላንድ ፊልም ታይቶ ውይይት እንደሚደረግበት ብሉ ናይል ፊልም እና ቴሌቪዥን አካዳሚ አስታወቀ፡፡ ስድስት ኪሎ ሐምሌ 19 መናፈሻ አካባቢ የሚገኘው አካዳሚ እንደገለፀው የኒኪ ካሮን “Whale Rider” ፊልም የሚያሳየው ከክሪስቶፍ ሞኒ ጋር በመተባበር ነው፡፡ ከሁለት ሳምንት በኋላ የፈረንሳይና የኢራን ፊልሞች በተመሳሳይ መልኩ እንደሚያሳይ ድርጅቱ ገልጿል፡፡
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና