ይህ በዚህ እንዳለ የአንጋፋው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም ተመሳሳይ አላማ ያለው ቢልቦርድ በመጪው ረቡዕ በባህር ዳር ከተማ ይመረቃል፡፡ አርቲስቱም ቢልቦርዱን ካዘጋጀው አይቴክ ኢትዮጵያ ጋር በመሆን ምርቃቱ ላይ ለመገኘት ወደ ባህር ዳር የሚጓዝ ሲሆን ተመሣሣይ የፀረ ቲቪ ቅስቀሳ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡ በሌላም በኩል አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም ባለፈው ረቡዕ ጉርድ ሾላ አካባቢ በሚገኘው ሉሲ ዩዝ አካዳሚ “ከበደ ሚካኤል የንባብና የውይይት ክበብ” በመገኘት የትምህርት ቤቱን ተማሪዎችና ወደ ትወና ጥበብ መግባት የሚፈልጉ ወጣቶችን በመምከር አበረታትቷል፡፡ አርቲስቱ በተጨማሪም ተጫውቷቸው ከነበሩ ተውኔቶች የሁለቱን ቃለ ተውኔት በመቀንጨብ ለተማሪዎቹ አስደምጧል፡፡ የትምህርት ቤቱ የንባብና የውይይት ክበብ፣ ባለፈው ወር ኢንጂነር ታደለ ብጡል ክብረትንና ጋዜጠኛ በፍቃዱ አባይን ጋብዞ የነበረ ሲሆን ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ኪነጥበባዊ ልምዳቸውን እንዳጋሩና ዝግጅቱ በየወሩ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል፡፡