ቴይለር ስዊፍት ለሂፕ ሆፕ አርቲስቷ ኒኪ ማናጅ አድናቆት እንዳላት ለኤምቲቪ ኒውስ ስትገልፅ አብራት ለመስራት እንደምትፈልግም ተናግራለች፡፡ የትሪንዳድና ቶቤጎ ደም ያላት የ28 አመቷ ኒኪ ማናጅ፤ በቢልቦርድ የአመቱ አዲስ ኮከብ አርቲስት ተብላ መመረጧን በደስታ የተቀበለች ሲሆን በ54ኛው ግራሚ ለአመቱ ምርጥ የራፕ ብቃትና ምርጥ የራፕ አልበም ዘርፎች ታጭታለች፡፡ የኒኪ ማናጅ አልበም “ ፒንክ ፍራይዴይ” ዘንድሮ በአሜሪካ ብቻ 1 ሚሊዮን 670 ሺህ ቅጂ ተቸብችቦ ከክሪስ ብራውንና ከሪሃና አልበሞች የተሻለ ገበያ እንዳገኘ ቢልቦርድ አመልክቷል፡፡