Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 December 2011 10:05

ጆርጅ ማይክል ክፉኛ ታሟል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በሳምባ ምች ታሞ ሆስፒታል የገባው ጆርጅ ማይክል፤ በሞት አፋፍ ላይ መሆኑ በስፋት ቢወራም ህክምናውን በተሳካ መንገድ እንዳደረገና እያገገመ እንደሆነ ታወቀ፡፡ የ48 አመቱ ጆርጅ ማይክል፤ በሳምባ ምች ብቻ ሳይሆን በሌሎች አሳሳቢ የጤና ችግሮች ደህነነቱ አደጋ ላይ መውደቁን የጠቆሙ ምንጮች፤ ቪዬና በሚገኝ ሆስፒታል ከፍተኛ የህክምና ክትትል ላይ እንደሆነና ባለሙያዎች ህይወቱን ለማትረፍ እየተረባረቡ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ በድንገተኛው ሁኔታ ጆርጅ ማይክል በኦስትሪያ ዋና ከተማ ሊያቀርብ የነበረውን ዝግጅት በህመም የተነሳ እንደሰረዘ ለኤቢሲ ኒውስ የገለፀው ቃል አቀባዩ፤ ያጋጠመው ህመም ህይወቱን አደጋ ላይ ጥሎታል በሚል የተናፈሱ ወሬዎችን “አሳፋሪ ውሸቶች” ሲል አጣጥሏቸዋል፡፡ በሙሉ ስሙ ጆርጂስ ካያሪኮስ ፓናጊዮቱ ተብሎ የሚታወቀው ጆርጅ ማይክል፤ በፖፕ ሮክ የሙዚቃ ስልት ላለፉት 30 አመታት በማቀንቀን ይታወቃል፡፡ ለገበያ ባበቃቸው 5 አልበሞች በመላው አለም 100 ሚሊዮን ቅጂዎች የቸበቸበው ጆርጅ ማይክል፤ የሃብት መጠኑ 140 ሚሊዮን ዶላር ይገመታል፡፡ አርቲስቱ ሆስፒታል ከገባ ሁለት ሳምንቱ ሲሆን አዲሱን የፈረንጆች አመት በሆስፒታሉ እንደሚያሳልፍ ተገምቷል፡፡

Read 3258 times