Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 December 2011 10:06

የአዳም ሳንድለር “አስቂነት” ቀንሷል ተባለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ባለፉት 13 አመታት በሰራቸው ኮሜዲ ፊልሞች በመላው አለም ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ያስገባው አዳም ሳንድለር፤ በቅርቡ በሰራቸው ፊልሞቹ የኮሜዲ ችሎታው ቀንሷል በሚል ትችት እንደበዛበት የካናዳው ጋዜጣ “ዘ ቫንኮቨር ሰን” ዘገበ፡፡ ዘንድሮ “ጀስት ጎ ዊዝ ኢት”፤ “ዙ ኪፐር” እና “ ጃክ ኤንድ ጂል” የተባሉ ኮሜዲ ፊልሞቹን ለእይታ ያበቃው አዳም ሳንድለር፤ በገቢ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቢሳካለትም የኮሜዲ ሥራዎቹ ተቀባይነት እየቀነሰ መጥቷል ተብሏል፡፡ አንዳንድ ተመልካቾች የችሎታው መቀነስ ከእድሜው መግፋት ጋር በተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ገምተዋል፡፡ የ45 ዓመቱ አዳም ሳንድለር በፊልም ሃያሲያን የትወና ብቃቱ ወርዷል ተብሎ በስፋት ሲተች ቢቆይም በቅርብ ጊዜ ለእይታ የበቁ ፊልሞቹ በገበያው ስኬታማ እንደነበሩ ይታወቃል፡፡ ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ለእይታ የበቁት ሶስት ፊልሞቹ እያንዳንዳቸው በአማካይ ከ120 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቶባቸዋል፡፡

Read 2769 times