Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 December 2011 10:12

“ከአድማስ ፊት” ኪነጥበባዊ ዝግጅቱን አቀረበ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በሻሸመኔ ከተማ ኪነጥበብ አፍቃሪዎች የተቋቋመው “ከአድማስ ፊት” የኪነጥበብ ማህበር 34ኛ ዝግጅቱን ባለፈው እሁድ በሻሸመኔ ከተማ አቀረበ፡፡ የኪነጥበብ ተሰጥኦ ያላቸው ጥበብ አፍቃሪዎች ችሎታቸውን ለሕዝብ እያቀረቡ እንዲያዳብሩና የአካባቢውን ሕብረተሰብ የጥበብ ፍላጎት ለማሟላት ከአመታት በፊት የተቋቋመው ማህበር ከኪነጥበባዊ ዝግጅቶቹ ባሻገር የኪነጥበብ እንግዶች በመጋበዝ ለአባላቱ ልምድ የሚያጋራ ሲሆን ባለፈው እሁድም ኮሜድያን ክበበው ገዳን እንግዳ አድርጓል፡፡ ከኮሜድያኑ በፊት እንግዶች ከነበሩት መካከልም ጋዜጠኛ ደረጄ ኃይሌ፣ አርቲስት ሽመልስ አበራ፣ አርቲስት ተስፋዬ አበበና ሌሎች ከአርባ በላይ ታዋቂ ግለሰቦች ይገኙበታል፡፡

Read 3644 times