Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 December 2011 10:13

ለዘሪቱ መታከሚያ የሙዚቃ ድግስ ሊቀርብ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከቅርብ አመታት ወዲህ በደም ቧንቧ ጥበት እና በነርቭ ሕመም እየተሰቃየች ያለችውን አንጋፋ ድምፃዊት ዘሪቱ ጌታሁን ለመታደግ እና መታከሚያ ገንዘብ ለማሰባሰብ የሙዚቃ ድግስ ተዘጋጀ፡፡ የዛሬ ሳምንት ከምሽቱ 12 ሰዓት በግሎባል ሆቴል በሚቀርበው ዝግጅት ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወረቅ፣ ድምፃዊት ፀደንያ ገብረማርቆስ፣ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ፣ ድምፃዊ ስለሺ ደምሴ፣ ኮሜድያን ክበበው ገዳና ሌሎችም በነፃ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡ ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ተወዳጅ ዘፈኖችን ስታቀርብ የነበረችው ዘሪቱ የ10 ዓመት ሕፃን ሆና ዘርፉን መቀላቀሏን ማወቅ ተችሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በወር 210 ብር ወርሃዊ የጡረታ አበል አውቶብስ ተራ አካባቢ ቀበሌ ቤት ውስጥ የምትኖረው አርቲስቷ፤ “ትዝታ በፖስት”፣ “እንቁጣጣሽ” “እቴ ያገሬ ልጅ” በሚሉት የዘፈን ሥራዎቿ እንዲሁም በትያትር ሥራዎቿ ትታወቃለች፡፡

Read 4385 times