Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 December 2011 12:26

ለሴካፋ ዋንጫ ኡጋንዳና ሩዋንዳ ይፋጠጣሉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ለ35ኛው የሴካፋ ታስከር ሲኒዬርስ ቻሌንጅ ካፕ ዛሬ በዳሬሰላም ሲጠናቀቅ ለደረጃ ሱዳን ከታንዛኒያ እንዲሁም ኡጋንዳና ሩዋንዳ ለዋንጫ ይጫወታሉ፡፡ የሴካፋ ዋንጫን ለ11 ጊዜያት በመውሰድና ለ34ኛ ጊዜ ተሳትፎ በማድረግ የሚመራው የኡጋንዳ ብሔራዊ ቡድን በ15 ጊዜ ተሳትፎ 1ጊዜ ዋንጫ የወሰደውን የሩዋንዳ ቡድን እንደሚያሸንፍ ተገምቷል፡፡ በአፍሪካ እግር ኳስ በምስራቅና በደቡብ አፍሪካ ያሉ ክለቦችን በማሰልጠን የ10 አመታት ልምድ ያለው ሚቾ በሩዋንዳ አሰልጣኝነት በብሄራዊ ቡድን ደረጃ ከጅምሩ ያስመዘገበው ስኬት አድናቆት አትርፎለታል፡፡ የሴካፋ ምክር ቤት ለዋንጫው አሸናፊ 30ሺ ዶላር ለሁለተኛ 20ሺ ብር እንዲሁም ለ3ኛ ደረጃ 10ሺ ዶላር እንደሚበረከት አስታውቋል፡፡

Read 3355 times