Saturday, 10 May 2014 13:14

“የሉሲ ከዋክብትና ሌሎችም” ለንባብ በቃ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

    በደራሲ ገብረክርስቶስ ኃይለስላሴ የተዘጋጀው “የሉሲ ከዋክብትና ሌሎችም” የተሰኘ የልጆች መልካም ሥነምግባር ማስተማርያ መፅሐፍ ታትሞ ለንባብ በቃ፡ አንጋፋው ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ በመጽሐፉ ጀርባ ላይ በሰጠው አስተያየት፤ “በየምዕራፉ የተካተቱት ጣፋጭ ታሪኮች ለልጆችም ሆነ ለአዋቂዎች ሰፊ ትምህርት ይሰጣሉ፡፡ ግብረገባዊነትንና መልካም ዜግነትንም ያላብሳሉ” ብሏል፡፡ “ቀደም ሲል ከጓደኛቸው ጋር ያሰናዱት “ናብሊስ” የተሰኘ የመልካም ሥነምግባር መጽሐፍ፤ ከ5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች፣ የሥነምግባርና የሥነ ዜጋ ትምህርት ማጣቀሻ ሆኖላቸዋል” ብለዋል - ደራሲው በአዲሱ መጽሐፋቸው መግቢያ ላይ፡፡ መጽሐፉ በ30 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲ ገብረክርስቶስ፤ ከዚህ ቀደም “ቅንጅት ከየት ወደየት”፣ “እምዬ” የተሰኘ የረዥም ልብወለድ፣ “በፈተናና በጥረት የታጀበ ስኬት” የሚል የህይወት ታሪክ እና “መቀናጆ” የሚል ርዕስ ያለው የግጥም መድበል ለአንባቢያን አቅርበዋል፡፡

Read 1532 times