Saturday, 17 May 2014 15:09

ከሳዑዲ የተባረሩ ስደኞች ተመልሰው እየሄዱ ነው

Written by 
Rate this item
(3 votes)

በአንድ ወር ከ700 በላይ ስደተኞች ድንበር ሲያቋርጡ ተይዘዋል አብዛኞቹ ተባርረው የመጡ ናቸው

      በሶማሌ ላንድ በኩል ቀይ ባህርን በጀልባ ተሻግረው ወደ ሳዑዲ አረቢያና ወደ የመን ለመሄድ ጉዞ የጀመሩ ከ700 በላይ ወጣቶች ሀረር አካባቢ እንደተያዙ የክልሉ ፖሊስ ገለፀ፡፡ ከ700 በላይ የሚሆኑት የተያዙት በአንድ ወር ውስጥ መሆኑን የጠቀሱት የሐረሪ ክልል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር ጣሰው ቻለው ለአዲስ አድማስ እንደገለጹት አብዛኞቹ ከ4ወር በፊት የሳዑዲ አረቢያ ከሳዑዲ የተባረሩ ስደኞች ተመልሰው እየሄዱ ነው በአንድ ወር ከ700 በላይ ስደተኞች ድንበር ሲያቋርጡ ተይዘዋል አብዛኞቹ ተባርረው የመጡ ናቸው መንግስት ህገወጥ ናችሁ በሚል ወደ ኢትዮጵያ የመለሳቸው ናቸው፡፡

ወጣቶች ከባሌ፣ ከጅማ፣ ከአርሲ፣ ከትግራይ ክልል ከተሞችና፣ ከደሴ በመነሳት ለህገወጥ አስኮብላዮች እስከ 5ሺ ብር በመክፈል በቅብብሎሽ ከከተማ ከተማ የተሸጋገሩ ሃረር የደረሱ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ፖሊስ፣ የህገወጥ ስደት ሰንሰለቱ ቦሳሶ ድንበርን በመሻገር በጀልባ ከ40 ሠዓት በላይ በመጓዝ ሳዑዲ አረቢያና የመን ድረስ እንደሚዘልቅ ፖሊስ አስረድቷል፡፡ ህገወጥ ስደትን መከላከል የፖሊስ የእለት ተእለት ስራ እየሆነ መምጣቱን የጠቆሙት ሃላፊው፤ ከሐረር ከተማ ወጣቶችን በድብቅ በአይሱዙ በመጫን ወደ ሶማሌ ላንድ የሚያጓጉዙ ህገወጥ ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እያዋሉ ነው፤ በሚያዚያ ወር ግን ህገወጥ የስዎች ዝውውር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ብለዋል፡፡ በሶማሌ ላንድ በኩል ባህሩን ለማቋረጥ በጀልባ ቀንና ሌሊቱን የሚደረገው ጉዞ እንደሆነ የጠቆመው ፖሊስ፣ ሰሞኑንም 80 ሰዎችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ ጀልባ ተገልብጦ በርካታ ስደተኞች ህይወት ማለፉን አስታውሷል፡፡ በየዕለቱ ከአራት በላይ ጀልባዎች ህገወጥ ስደተኞችን በመጫን ወደ የመን ድንበር እንደሚደርሱና አንድ ጀልባ ከ80 እስከ 90 የሚደርሱ ስደተኞች እንደሚጫንም ገልጸዋል፡፡

Read 4329 times