Saturday, 24 May 2014 13:27

የኢትዮጵያ ምርቶች የሚቀርቡበት የንግድ ትርኢት በአሜሪካ ሊዘጋጅ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የአልባሳት፣ የጨርቃጨርቅ እና የእግር ሹራብ አምራቾችንና ነጋዴዎችን በአንድነት ያሰባስባል የተባለ የንግድ ሣምንት ከነሐሴ 11-14 2006 ዓ.ም በአሜሪካን ላስቬጋስ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ገለፁ፡፡
አለማቀፍ የፋሽን ድርጅቶች ይሳተፉበታል የተባለው የንግድ ሣምንት አለማቀፍ የፋሽን ማህበረሰቡን በማቀራረብ ሰፊ ግብይት ይፈፀምበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ የዝግጅት አስተባባሪ የ251 ኮሚኒኬሽንና ማርኬቲንግ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ አዲስ አለማየሁ ገልፀዋል፡፡
አክለውም በዝግጅቱ ላይ የኢትዮጵያ አልባሣት፣ ጨርቃጨርቅ እና ጫማ አምራቾች እንደሚሳተፉና ከ100 ሃገራት ከተውጣጡት የንግድ ሳምንቱ ተሳታፊ ኩባንያዎች ጋር የረዥም ጊዜ ግንኙነት ይፈጥራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡
የንግድ ትርኢቱ ከ6 ሺህ በላይ የሚሆኑ የምርት አይነቶች የሚቀርቡበት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ የ251 ኮሚኑኬሽን ተባባሪ የሆነው ማጂክ ኢንተርናሽናል የአለማቀፍ ቢዚነስ ኃላፊ ቦብ በርግ በበኩላቸው በዘርፉ የተሰማሩ የኢትዮጵያ ፋብሪካዎች ከንግድ ትርኢቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል፡፡
በንግድ ትርኢቱ ላይ ይሳተፋሉ ተብለው ለሚጠበቁ የኢትዮጵያ የቆዳ ኢንዱስትሪ ማህበር፣ ለኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ አምራች ማህበራት እና ለUSAID እንዲሁም ለአሜሪካ ኤምባሲ የፕሮግራም አዘጋጆች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡  

Read 1654 times