Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 December 2011 09:51

የርዕዮተ - ዓለም ጨዋታ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

2011-12-17

ፋሺስት - ሁለት ላሞች አሉህ፡፡ መንግስት ሁለቱንም ይወስዳቸውና ወተቱን ይሸጥልሃል፡፡ አንተ ከህቡዕ ድርጅት ጋር ትቀላቀልና የመንግስት ንብረት የማውደም ሴራ ላይ በንቃት ትሳተፋለህ፡፡
የአሜሪካን ኮርፖሬሽን - ሁለት ላሞች አሉህ፡ አንዷን ትሸጥና ሌላኛዋ የአራት ላሞች ወተት እንድትሰጥህ ታስገድዳታለህ፡፡ ላምዋ ስትሞት ትገረማለህ፡፡
የፈረንሳይ ኮርፖሬሽን - ሁለት ላሞች አሉህ፡፡ ሦስት ላሞች እፈልጋለሁ ትልና አድማ ትመታለህ፡፡
የጃፓን ኮርፖሬሽን - ሁለት ላሞች አሉህ፡፡ አካላቸውን አሻሽለህ በመሥራት ከተለመዱት ላሞች የአካል መጠን 1/10ኛ ያህል ብቻ እንዲሆኑና 20 እጅ የሚበልጥ ወተት እንዲሰጡ ታደርጋቸዋለህ፡ ከዚያም ብልህ የሚመስሉ የላሞች ምስል በካርቱን ታሰራና “Cow kimon” የሚል ስም ትሰጣቸዋለህ፡፡ በመጨረሻም በመላው ዓለም ለገበያ ታስተዋውቃቸዋለህ፡፡
የህንድ ኮርፖሬሽን - ሁለት ላሞች አሉህ፡፡ ሁለቱንም ለአምልኮ ትጠቀምባቸዋለህ፡፡
የቻይና ኮርፖሬሽን - ሁለት ላሞች አሉህ፡ ላሞቹን የሚያልቡ 300 ሰዎች ይኖሩሃል፡፡ ከዚያም ሁሉም ሰው የሥራ እድል እንደተፈጠረለት ትደሰኩራለህ፡፡ ይሄን ከእውነት የራቀ ዲስኩር ያጋለጡትን ጋዜጠኞች እያስያዝክ ወህኒ ቤት ትወረውራለህ፡፡
የስዊስ ኮርፖሬሽን - 500 ላሞች አሉህ፤ አንዳቸውም ግን ያንተ አይደሉም፡፡ ሌሎች አንተ ጋ ላስቀመጡበት ታስከፍላለህ፡፡ (ባንኮችን ይሆን?)
የብራዚል ኮርፖሬሽን - ሁለት ላሞች አሉህ፤ ሁለቱን ይዘህ ከአሜሪካ ኮርፖሬሽን ጋር ሽርክና ትገባለህ፡፡ ወዲያው 1000 ላሞች ይሆኑልሃል፡፡ እናም የአሜሪካው ኮርፖሬሽን መክሰሩን ያውጃል፡፡
የሩሲያ ኮርፖሬሽን - ሁለት ላሞች አሉህ፡ ስትቆጥራቸው አምስት መሆናቸውን ትረዳለህ፡፡ እንደገና ስትቆጥራቸው 42 ይሆኑብሃል፡፡ አሁንም ትቆጥራቸዋለህ፤ 12 ናቸው፡፡ መቁጠሩን ትተውና ሌላ ቮድካ ትከፍታለህ፡፡

ሶሻሊስት - ሁለት ላሞች አሉህ፡፡ መንግስት አንደኛዋን ላም ይቀማህና ለጐረቤትህ ይሰጥብሃል፡፡

ኮሙኒስት - ሁለት ላሞች አሉህ፡፡ ሁለቱንም መንግስት ይወስድብህና ወተት ይሰጥሃል፡፡

የአሜሪካ ሪፐብሊካን - ሁለት ላሞች አሉህ፡፡ ጐረቤትህ ግን ምንም የለውም፡፡ “እና ምን ይጠበስ” ይልሃል፡፡

ክርስትያን ዲሞክራት - ሁለት ላሞች አሉህ፡ ማንም ሳይጠይቅህ “አንዱ ይበቃኛል” ትልና አንደኛዋን ለጐረቤትህ ትሰጣለህ

የአሜሪካ ዲሞክራት - ሁለት ላሞች አሉህ፡ ጐረቤትህ ግን ምንም የለውም፡፡ ስኬታማ በመሆንህ ትፀፀታለህ፡ እናም በላሞችህ ላይ ግብር ለሚጥሉ ሰዎች ድምጽ ትሰጣለህ፡፡ ከዚያም ለግብር የምትከፍለውን ገንዘብ ለማግኘት ስትል አንዷን ላምህን ለመሸጥ ትገደዳለህ፡ በድምጽህ የመረጥካቸው ሰዎች የግብር ገንዘቡን ካንተ ላይ ይወስዱና አንዲት ላም ገዝተው ለጐረቤትህ ይሰጡታል፡፡ አንተም ፃድቅነት ይሰማሃል፡

ፋሺስት - ሁለት ላሞች አሉህ፡፡ መንግስት ሁለቱንም ይወስዳቸውና ወተቱን ይሸጥልሃል፡፡ አንተ ከህቡዕ ድርጅት ጋር ትቀላቀልና የመንግስት ንብረት የማውደም ሴራ ላይ በንቃት ትሳተፋለህ፡፡

የአሜሪካን ኮርፖሬሽን - ሁለት ላሞች አሉህ፡ አንዷን ትሸጥና ሌላኛዋ የአራት ላሞች ወተት እንድትሰጥህ ታስገድዳታለህ፡፡ ላምዋ ስትሞት ትገረማለህ፡፡

የፈረንሳይ ኮርፖሬሽን - ሁለት ላሞች አሉህ፡፡ ሦስት ላሞች እፈልጋለሁ ትልና አድማ ትመታለህ፡፡

የጃፓን ኮርፖሬሽን - ሁለት ላሞች አሉህ፡፡ አካላቸውን አሻሽለህ በመሥራት ከተለመዱት ላሞች የአካል መጠን 1/10ኛ ያህል ብቻ እንዲሆኑና 20 እጅ የሚበልጥ ወተት እንዲሰጡ ታደርጋቸዋለህ፡ ከዚያም ብልህ የሚመስሉ የላሞች ምስል በካርቱን ታሰራና “Cow kimon” የሚል ስም ትሰጣቸዋለህ፡፡ በመጨረሻም በመላው ዓለም ለገበያ ታስተዋውቃቸዋለህ፡፡

የህንድ ኮርፖሬሽን - ሁለት ላሞች አሉህ፡፡ ሁለቱንም ለአምልኮ ትጠቀምባቸዋለህ፡፡

የቻይና ኮርፖሬሽን - ሁለት ላሞች አሉህ፡ ላሞቹን የሚያልቡ 300 ሰዎች ይኖሩሃል፡፡ ከዚያም ሁሉም ሰው የሥራ እድል እንደተፈጠረለት ትደሰኩራለህ፡፡ ይሄን ከእውነት የራቀ ዲስኩር ያጋለጡትን ጋዜጠኞች እያስያዝክ ወህኒ ቤት ትወረውራለህ፡፡

የስዊስ ኮርፖሬሽን - 500 ላሞች አሉህ፤ አንዳቸውም ግን ያንተ አይደሉም፡፡ ሌሎች አንተ ጋ ላስቀመጡበት ታስከፍላለህ፡፡ (ባንኮችን ይሆን?)

የብራዚል ኮርፖሬሽን - ሁለት ላሞች አሉህ፤ ሁለቱን ይዘህ ከአሜሪካ ኮርፖሬሽን ጋር ሽርክና ትገባለህ፡፡ ወዲያው 1000 ላሞች ይሆኑልሃል፡፡ እናም የአሜሪካው ኮርፖሬሽን መክሰሩን ያውጃል፡፡

የሩሲያ ኮርፖሬሽን - ሁለት ላሞች አሉህ፡ ስትቆጥራቸው አምስት መሆናቸውን ትረዳለህ፡፡ እንደገና ስትቆጥራቸው 42 ይሆኑብሃል፡፡ አሁንም ትቆጥራቸዋለህ፤ 12 ናቸው፡፡ መቁጠሩን ትተውና ሌላ ቮድካ ትከፍታለህ፡፡

Read 4924 times Last modified on Saturday, 17 December 2011 09:54