Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 17 December 2011 10:08

የሃሪ ፖተር 8ኛ ፊልም የዓመቱን ከፍተኛ ገቢ አገኘ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በሆሊውድ ተሰርተው ለእይታ ከበቁ የዘንድሮ ፊልሞች በተከታታይ ክፍል የቀረቡ፤ በአፈታሪክ ጭብጦች ላይ የሚያጠነጥኑ እና የካርቱንና የአኒሜሽን ፊልሞች ከፍተኛ ገቢ እንዳገኙ “ቦክስ ኦፊስ ሞጆ” አመለከተ፡፡  ዘንድሮ ሆሊውድ በአለም አቀፍ ገበያ 36.8 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ያገኘ ሲሆን ገቢው ባለፉት ሦስት ዓመታት ከተመዘገበው በ10 በመቶ እንደቀነሰ ተጠቆመ፡፡ በዓመቱ ከ570 በላይ ፊልሞች የወጡ ሲሆን ከፍተኛ ገቢ ከተገኘባቸው 10 ፊልሞች ስምንቱ በተከታይ ክፍል የቀረቡ  ናቸው፡፡ የሃሪ ፖተር 8ኛ ፊልም “ሃሪ ፖተር ኤንድ ዘ ዴዝሊ ሃውሎስ” 1.33 ቢሊዮን ዶላር ያስገባ ሲሆን የዓመቱን ከፍተኛ ገቢ በማግኘት የመሪነቱን ደረጃ ይዟል፡፡ “ትራንስፎርመርስ፡ ዳርክ ሳይድ ኦፍ ዘ ሙን” በ1.1 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም “ፓይሬትስ ኦፍ ካረቢያን፡ ኦን ስትሬንጀር ታይድስ” በ1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተከታታይ ደረጃን ይዘዋል - በገቢ፡፡

 

 

Read 2452 times Last modified on Saturday, 17 December 2011 10:16

Latest from