Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 17 December 2011 10:17

የዱባይ የፊልም ፌስቲቫል በቶም ክሩዝ አዲስ ፊልም ተጀመረ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

“8ኛው የዱባይ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል” ሰሞኑን በዱባይ እየተካሄደ ሲሆን ከሆሊውድና ከቦሊውድ በርካታ የፊልም ባለሙያዎችን እንደሳበ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ፌስቲቫሉ ሰሞኑን የተጀመረው በቶም ክሩዝ “ሚሽን ኢምፖሲብል ዘ ገስት” የተሰኘ አዲስ ፊልም ምረቃ ሲሆን ቶም ክሩዝ በፊልሙ በዱባይ ከተማ የሚገኘውንና የዓለማችን ግዙፍ ህንፃ የሆነውን “ቡርጃ ካሊፋ” በመውጣት ያሳየው ጀብዱ መነጋገርያ እንደሆነ ታውቋል፡፡የ49 ዓመቱ ቶም ክሩዝ ለሦስት ጊዜ ያህል ለኦስካር ሽልማት የታጨና በ”ምርጥ ተዋናይነት” ሶስት የጎልደን ግሎብ ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን በሶስቱ የ”ሚሽን ኢምፖስብል” ፊልሞች በአጠቃላይ 1.2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝቷል፡፡በዱባይ እየተካሄደ ባለው የፊልም ፌስቲቫል በወቅቱ የዓረቡ ዓለም አብዮት ዙርያ ያጠነጠኑ ጥናታዊና አጫጭር ፊልሞች የቀረቡ ሲሆን በተለይ የግብፅን ህዝባዊ አመፅ የሚዳስሱ ፊልሞች እንደታዩ ታውቋል፡፡

“ፕራይስ ኦፍ ዘ ኪንግስ” በሚል በቀድሞው የፍልስጤም መሪ ያሲን አራፋት የህይወት ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራው ባለ 12 ክፍል ዶክመንታሪ ፊልምም ከፍተኛ ትኩረት አግኝቷል ተብሏል፡፡ በፊልም ፌስቲቫሉ ከ56 አገራት የተሰባሰቡ 171 ፊልሞች ለእይታ ቀርበዋል፡፡“8ኛው የዱባይ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል” ሰሞኑን በዱባይ እየተካሄደ ሲሆን ከሆሊውድና ከቦሊውድ በርካታ የፊልም ባለሙያዎችን እንደሳበ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ፌስቲቫሉ ሰሞኑን የተጀመረው በቶም ክሩዝ “ሚሽን ኢምፖሲብል ዘ ገስት” የተሰኘ አዲስ ፊልም ምረቃ ሲሆን ቶም ክሩዝ በፊልሙ በዱባይ ከተማ የሚገኘውንና የዓለማችን ግዙፍ ህንፃ የሆነውን “ቡርጃ ካሊፋ” በመውጣት ያሳየው ጀብዱ መነጋገርያ እንደሆነ ታውቋል፡፡  የ49 ዓመቱ ቶም ክሩዝ ለሦስት ጊዜ ያህል ለኦስካር ሽልማት የታጨና በ”ምርጥ ተዋናይነት” ሶስት የጎልደን ግሎብ ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን በሶስቱ የ”ሚሽን ኢምፖስብል” ፊልሞች በአጠቃላይ 1.2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝቷል፡፡  በዱባይ እየተካሄደ ባለው የፊልም ፌስቲቫል በወቅቱ የዓረቡ ዓለም አብዮት ዙርያ ያጠነጠኑ ጥናታዊና አጫጭር ፊልሞች የቀረቡ ሲሆን በተለይ የግብፅን ህዝባዊ አመፅ የሚዳስሱ ፊልሞች እንደታዩ ታውቋል፡፡ “ፕራይስ ኦፍ ዘ ኪንግስ” በሚል በቀድሞው የፍልስጤም መሪ ያሲን አራፋት የህይወት ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራው ባለ 12 ክፍል ዶክመንታሪ ፊልምም ከፍተኛ ትኩረት አግኝቷል ተብሏል፡፡ በፊልም ፌስቲቫሉ ከ56 አገራት የተሰባሰቡ 171 ፊልሞች ለእይታ ቀርበዋል፡፡

 

 

 

Read 3941 times Last modified on Saturday, 17 December 2011 10:33

Latest from