Saturday, 31 May 2014 14:14

አዲዲሶቹ ወጣት ቢሊየነሮች

Written by  መንግሥቱ አበበ
Rate this item
(1 Vote)

የሶፍትዌር እውቀት በየእለቱ ቱጃሮችን ይፈጥራል ብንል ይሻላል፡፡ የሁለት ኢንተርፕረነሮችን ታሪክ ላጫውታችሁ፡፡ ማይክ ካኖን ብሩክስ እና ስኮት ፍራከር ይባላሉ፡፡ ሁለቱ አውስትራላውያን ወጣቶች የሶፍትዌር ባለሙያ ናቸው፡፡  በጋራ የመሰረቱት አትላሲያን የተባለ የሶፍትዌር ኩባንያ 3.3 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ እንዳለው ከታወቀ በኋላ ለእያንዳንዳቸው የ1.1 ቢሊዮን ዶላር ድርሻ ስላጎናፀፋቸው የቢሊየነሮችን ክለብ መቀላቀል ችለዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያሉ የተገናኙት ሁለቱ ወጣቶች፤ በ10ሺ ዶላር ብድር በሽርክና የሶፍትዌር ቢዝነስ የጀመሩት ከ12 ዓመት በፊት ነው፡፡ የሥራ ሂደት ማኔጅመንት (Workflow-management) የተባለውን ፕሮጀክታቸውን እንደፌስቡክ፣ ሲስኮስና ሲቲ ግሩፕ፣ ቢኤምደብሊው (BMW) የመሳሰሉ ታላላቅ ኩባንያዎችን ጨምሮ 35ሺ ኩባንያዎች እየተጠቀሙበት ነው፡፡
የኢንተርፕረነሮቹ ምርት በማስታወቂያ ብዛት የታጀበ አልነበረም፡፡ ዝም ብለው ምርታቸውን በዌብ ሳይታቸው ነው የሸጡት፡፡ አሁን ይሄው ቢሊየነሮች ሆነዋል፡፡

Read 1999 times