Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 December 2011 09:01

ማይክል ቡብሊ የገና ገበያን ይመራል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

“ክሪስትማስ” የተባለውን አዲስ አልበሙን ከሁለት ወር በፊት የለቀቀው ካናዳዊ ድምፃዊ ማይክል ቡብሊ፤ የቢልቦርድን የምርጥ 200 አልበሞች የደረጃ ሠንጠረዥ በከፍተኛ ሳምንታዊ ሽያጭ እየመራ መሆኑ ታወቀ፡፡ የቢልቦርድ መጽሔት ዘገባ እንዳመለከተው የማይክል ቡብሊ “ክሪስማስ” በዚህ ሳምንት 479ሺ ቅጂ ተሸጧል፡፡ ባለፉት አራት ሳምንታት በአጠቃላይ 1.96 ሚሊዮን ቅጂ የተሸጠው “ክሪስማስ” በዓመቱ በአሜሪካ ከፍተኛ ሽያጭ ካስመዘገቡ አልበሞች 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ በ2011 ከወጡ አልበሞች የዓመቱን ከፍተኛ ሽያጭ በሰሜን አሜሪካ በማስመዝገብ በአንደኛነት የምትመራው “21” የተሰኘ አልበም ያወጣቸው አዴሌ ስትሆን የሌዲ ጋጋ “ቦርን ዚስ ዌይ” በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡  ማይክል ቡብሊ ሦስት የግራሚ ሽልማቶችን  ያሸነፈ ሲሆን አስቀድሞ ለገበያ ያቀረባቸው  አራት አልበሞቹ በዓለም ዙሪያ 30 ሚሊዮን ቅጂ ተሸጦለታል፡፡

 

 

 

Read 1816 times Last modified on Saturday, 24 December 2011 09:05