እድሜአቸው ከሁለት እስከ 10 ዓመት የሆኑ ሃያ ሶስት ሕፃናት የተሳተፉበት የ45 ደቂቃ “ጨረቃ ድንቡል ዶቃ” ቪሲዲ ትናንት ማታ በሒልተን ተመረቀ፡፡ አራት ነባር ዜማዎችንና ስድስት የፈጠራ ስራዎችን የያዘውን ቪሲዲ፤ በሕይወት ችልድረን ሶንግ ፕሮዳክሽን የተዘጋጀ ነው፡፡ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ሕይወት ማሞ ቪሲዲውን አስመልክቶ ሲናገሩ፤ ስልጠናን ጨምሮ ለማዘጋጀት 18 ወራት መፍጀቱንና ልጆች በቀላሉ እየተዝናኑ ባህላቸውን እንዲያውቁ መታለሙን ተናግረዋል፡፡ ወ/ሮ ሕይወት ማሞ የልጅነት ሕይወትን አስመልክቶ መፃሕፍትና መዝሙሮች በማዘጋጀት እንዲሁም ሕፃናትን ፒያኖ በማስተማር እንዲሁም ከለር የሚቀቡ የሕፃናት መፃሕፍት በማዘጋጀት ትታወቃለች፡፡