Print this page
Saturday, 16 August 2014 10:13

ኒው ጄኔሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተማሪዎቹን ያስመርቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ኒው ጄኔሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 284 ተማሪዎች ዛሬ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በአፍሪካ ህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ያስመርቃል፡፡ ከተማሪዎቹ ምርቃት በተጨማሪ ከዘጠኙ ክልሎች በማስተማር ክህሎታቸው የላቀ ብልጫ ያሳዩ የኢትዮጵያ መምህራን እንደሚሸለሙ ኒው ጄኔሬሽን አስታውቋል፡፡ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ዘንድሮ የሚያስመርቃቸው በአካውንቲንግ ኤንድ ፋይናንስ፣ በቢዝነስ አድምኒስትሬሽን፣ በኮምፒዩተር ሳይንስ እና በሂውማን ሪሶርስ ኤንድ ሊደርሺፕ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ተማሪዎችን እንደሆነ የዩኒቨርሲ ኮሌጁ መስራችና ፕሬዚዳንት አቶ ማቲዎስ ግችሌ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ከሶስት ሳምንታት በፊት በነቀምት ካምፓስ ከላይ የተጠቀሱትን ዘርፎች ጨምሮ በኮኦፕሬቲቭ አካውንቲንግ፣ በማህበረሰብ ጥናትና በማህበራዊ ሥነ-ሰብ እንዲሁም በነርሲንግ በዲግሪና በተለያዩ የቴክኒክና ሙያ ዘርፎች በጥቅሉ ወደ 700 ያህል ተማሪዎች ማስመረቁን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡
ኒውጄኔሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ዛሬ የሚያስመርቀው ለ11ኛ ጊዜ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ማቲዎስ፤ ባለፉት አስር ዙሮች በተለያየ ዘርፍ የሰለጠኑ 16 ሺህ ተማሪዎችን ማስመረቁን ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ቀደም ባሉት ዓመታት በኦሮሚያ የጀመረውን የኮከብ መምህራን ሽልማት ወደ አገር አቀፍ ደረጃ በማሳደግ፣ በዛሬው እለት ከዘጠኙም ክልሎች የተውጣጡና በማስተማር ክህሎታቸው የላቁ መምህራንን እንደሚሸልም አቶ ማቲዎስ ተናግረዋል፡፡

Read 1233 times