የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከኪነጥበብ ሙያ ማህበራት ጋር በመተባበር በአራት ዘርፎች የጥበብ ባለሙያዎችን አወዳድሮ ሊሸልም እንደሆነ ለአዲስ አድማስ ገለፀ፡፡
በድርሰት፣ ሙዚቃ፣ ስዕልና ፊልም ዘርፎች ለሚካሄደው ውድድር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከአገር አቀፍ የሙያ ማህበራት ጋር በመሆን ለየዘርፉ አስር እጩ ተሸላሚዎችን አቅርቧል፡፡
ከየዘርፉ ሦስት አሸናፊዋች የ”ሽልማት ለጥበብ 2006” ተሸላሚ እንደሚሆኑ የገለፀው ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፤ ህብረተሰቡ ከእያንዳንዱ ዘርፍ ሦስት (በደረጃ ቅደም ተከተል) እጩ ተሸላሚዎችን በSMS 8181 መስመር መምረጥ እንደሚችል አስታውቋል፡፡
በአገሪቱ የሚገኙ የኤሌክትሮኒክስና የህትመት ሚዲያዎችም ከየዘርፉ የሚመርጧቸውን እጩ ተሸላሚዎች በተላከላቸው ቅጽ ሞልተው እንደሚልኩ ታውቋል፡፡ ከየጥበብ ዘርፉ የተመረጡ ዳኞችም በምርጫው የሚሳተፉ ሲሆን የሦስቱ ወገኖች ነጥብ ተደምሮ አሸናፊዎቹ እንደሚለዩ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የላከው መግለጫ ይጠቁማል፡፡
ለኪነጥበብ ባለሙያዎች እውቅና በመስጠት ጥበብን የሚያበረታታ ነው የተባለው ሽልማት በመጪው ጳጉሜ 1 ለአሸናፊዎች እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በስዕልና ቅርፃ ቅርጽ ዘርፍ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ድምጽ መስጫ ቅጽ
ስም የSMS ቁጥር ድምጽ
መዝገቡ ተሰማ Vote 100
አለፈለገ ሰላም Vote 101
ኤልያስ ስሜ Vote 102
በቀለ መኮንን Vote 103
ዳዊት አበበ Vote 104
ወርቁ ጐሹ Vote 105
ሚካኤል ፀጋው Vote 106
ብስራት ሺባባው Vote 107
ታደሰ መስፍን Vote 108
አስኒ ጋለሪ Vote 109
በሙዚቃ ዘርፍ እጩ ተወዳዳሪዎች
ስም የSMS ቁጥር ድምጽ
አስቴር አወቀ Vote 200
ኩኩ ሰብስቤ Vote 201
ታደለ ገመቹ Vote 202
ፀጋዬ እሸቱ Vote 203
ሚካኤል በላይነህ Vote 204
ግርማ ተፈራ Vote 205
አብረሃም ገ/መድህን Vote 206
አበባ ደሳለኝ Vote 207
ጃሉድ አወል Vote 208
ቴዎድሮስ ካሳሁን Vote 209
በፊልም ዘርፍ እጩ ተወዳዳሪዎች
ስም የSMS ቁጥር ድምጽ
ዳይናማይት Vote 300
ያልታሰበው Vote 301
ቀሚስ የለበስኩ’ለት Vote 302
ረቡኒ Vote 303
አይራቅ Vote 304
ኒሻን Vote 305
400 ፍቅር Vote 306
ገዳይ ሲያረፍድ Vote 307
የሎሚ ሽታ Vote 308
የመጨረሻዋ ቀሚስ Vote 309
በስነፅሁፍ ዘርፍ እጩ ተወዳዳሪዎች
ስም የSMS ቁጥር ድምጽ
ደራሲ ይልማ ሀብተየስ Vote 400
ደራሲ መስፍን ሀብተማርያም Vote 401
ደራሲ ታደሰ ሊቨን Vote 402
ደራሲ ሀይለመለኮት መዋል Vote 403
ደራሲ ፀሐይ መላኩ Vote 404
ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ Vote 405
ደራሲ አያልነህ ሙላት Vote 406
ደራሲ የዝና ወርቁ Vote 407
ደራሲ ኢሳያስ ወርዶፋ Vote 408
ደራሲ አስፋው ዳምጤ Vote 419