Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 31 December 2011 10:25

የፖለቲካ ጥግ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ስለመንግስትና ፖለቲካ

  • የህዝብ ድምፅ የእግዚአብሔር ድምፅ ነው፡፡

አልኩይን

(የእንግሊዝ ካህን፣ የሥነ መለኮት ሊቅና ምሁር)ህዝቡ እየገዛሁ ነው ብሎ እንዲያስብ አድርገው፤  ያን ጊዜ ይገዛልሃል፡፡

ዊልያም ፔን

(እንግሊዛዊ ሰባኪና ቅኝ ገዢ)

 

 

  • ህዝብ የራሱን ቋንቋ በማይናገሩ ሰዎች ለመገዛት ፈቃደኛ አይደለም፡፡

ኖርማን ቴቢት

(እንግሊዛዊ ፖለቲካ)

  • የተወሰነ መደብ ህዝብን ለመግዛት ብቁ አለመሆኑ አይደለም አደጋው፤ ሁሉም መደብ ለመግዛት ብቁ አለመሆኑ እንጂ፡፡

ሎርድ አክተን

(እንግሊዛዊ የታሪክ ምሁር)

  • የመንግስት አራቱ ምሰሶዎች - ሃይማኖት፣ ፍትህ፣ ም/ቤትና ግምጃ ቤት ናቸው፡፡

ፍራንሲስ ቤከን

(እንግሊዛዊ ፈላስፋ፣ ፖለቲከኛና ጠበቃ)

  • ታላላቅ ሰዎች መገዛት አይችሉም፡፡

አየን ራንድ

(ትውልደ ራሽያ አሜሪካዊት ፀሐፊና ፈላስፋ)

  • መንግስት አሪፍ የሚሆነው በጥቂቱ ብቻ ሲገዛ ነው፡፡

(የአሜሪካውያን አባባል)

  • ሌሎችን የሚያስተዳድር ሰው መጀመሪያ የራሱ ጌታ መሆን አለበት፡፡

ፊሊፕ ማሲንጋር

(እንግሊዛዊ ፀሐፌ ተውኔት)

  • ኮሙኒዝም ተንኮታኩቷል፡፡ ካፒታሊዝም ግን አልተሳካለትም፡፡

ዊሊያም ኪጋን

(እንግሊዛዊ ደራሲና ጋዜጠኛ)

  • የኮሙኒስት አመራርን ለመቃወም የሚሞክር አዲስ ፓርቲ ከተፈጠረ እንዲኖር አይፈቅድለትም፡፡

ሊ ፔንግ

የቻይና ጠ/ሚኒስትር 1928)

  • የዲሞክራሲ ደዌዎች በሙሉ የሚፈወሱት በበለጠ ዲሞክራሲ ነው፡፡

አል ስሚዝ

(አሜሪካዊ ፖለቲከኛ)

  • ዲሞክራሲ ለእያንዳንዱ ሰው የራሱ ጨቋኝ የመሆን መብት ያጐናጽፈዋል፡፡

ጀምስ ረሰል ሎዌል

(አሜሪካዊ ገጣሚ፣ አርታኢ፣ ወግ ፀሐፊና ዲፕሎማት)

 

 

Read 3525 times Last modified on Saturday, 31 December 2011 10:33