- ህዝብ የራሱን ቋንቋ በማይናገሩ ሰዎች ለመገዛት ፈቃደኛ አይደለም፡፡
ኖርማን ቴቢት
(እንግሊዛዊ ፖለቲካ)
- የተወሰነ መደብ ህዝብን ለመግዛት ብቁ አለመሆኑ አይደለም አደጋው፤ ሁሉም መደብ ለመግዛት ብቁ አለመሆኑ እንጂ፡፡
ሎርድ አክተን
(እንግሊዛዊ የታሪክ ምሁር)
- የመንግስት አራቱ ምሰሶዎች - ሃይማኖት፣ ፍትህ፣ ም/ቤትና ግምጃ ቤት ናቸው፡፡
ፍራንሲስ ቤከን
(እንግሊዛዊ ፈላስፋ፣ ፖለቲከኛና ጠበቃ)
- ታላላቅ ሰዎች መገዛት አይችሉም፡፡
አየን ራንድ
(ትውልደ ራሽያ አሜሪካዊት ፀሐፊና ፈላስፋ)
- መንግስት አሪፍ የሚሆነው በጥቂቱ ብቻ ሲገዛ ነው፡፡
(የአሜሪካውያን አባባል)
- ሌሎችን የሚያስተዳድር ሰው መጀመሪያ የራሱ ጌታ መሆን አለበት፡፡
ፊሊፕ ማሲንጋር
(እንግሊዛዊ ፀሐፌ ተውኔት)
- ኮሙኒዝም ተንኮታኩቷል፡፡ ካፒታሊዝም ግን አልተሳካለትም፡፡
ዊሊያም ኪጋን
(እንግሊዛዊ ደራሲና ጋዜጠኛ)
- የኮሙኒስት አመራርን ለመቃወም የሚሞክር አዲስ ፓርቲ ከተፈጠረ እንዲኖር አይፈቅድለትም፡፡
ሊ ፔንግ
የቻይና ጠ/ሚኒስትር 1928)
- የዲሞክራሲ ደዌዎች በሙሉ የሚፈወሱት በበለጠ ዲሞክራሲ ነው፡፡
አል ስሚዝ
(አሜሪካዊ ፖለቲከኛ)
- ዲሞክራሲ ለእያንዳንዱ ሰው የራሱ ጨቋኝ የመሆን መብት ያጐናጽፈዋል፡፡
ጀምስ ረሰል ሎዌል
(አሜሪካዊ ገጣሚ፣ አርታኢ፣ ወግ ፀሐፊና ዲፕሎማት)