Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 31 December 2011 11:36

የዝውውር ገበያው ይቀዘቅዛል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በነገው እለት የሚከፈተው የአውሮፓ እግር ኳስ የተጨዋቾች የዝውውር ገበያ ቀዝቃዛ እንደሚሆን ተጠበቀ፡፡ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ የዝውውር ወቅት የወጣው 225 ሚሊዮን ፓውንድ ሲሆን ዘንድሮ ግማሹ እንኳን ወጪ እንደማይሆን መረጃዎች እየገለፁ ናቸው፡፡ ዴሊዮቴ በሰራው ጥናት በዘንድሮው የአዲስ ዓመት የዝውውር መስኮት የአውሮፓ ክለቦች የዝውውር ወጪ ቢበዛ 170 ሚሊዮን ቢያንስ 60 ሚሊዮን ፓውንድ ብቻ ቢሆን ነው፡፡

በውድድር ዘመኑ መግቢያ ላይ በተካሄደው የክረምቱ የዝውውር ገበያ ከፍተኛ ድርሻ የነበራቸው የእንግሊዝ ክለቦች ወጪያቸው 485 ሚሊዮን ፓውንድ እንደነበረ ሲታወስ የዚህን ግማሽ ያህል በአሁኑ የአዲስ ዓመት ግብይት ላይወጣበት እንደሚችል የተገመተው በተለያዩ ምክንያቶች ነው፡፡ በውድድር ዘመኑ መግቢያ ላይ እስከ 50 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ በማድረግ ተጨዋቾች የገዙት የእንግሊዝ ትልልቅ ክለቦች ነገ በሚከፈተው ገበያ ቡድናቸውን በሚያነቃቃ የዝውውር ወሬ ቢጠመዱ እንጅ ክፍያ በመፈፀም ለመሳተፍ በቂ የፋይናንስ አቅም የላቸውም ተብሏል፡፡በጥር ወር የዝውውር ገበያ ላይ በውሰት ውል ከክለብ ወደ ክለብ የሚሸጋገሩ ተጨዋቾች ይበዙበታል፡፡ በተለይ የአሜሪካ ሜጀር ሶከር ሊግ ነገ ከመዘጋቱ ጋር በተያያዘ እነደ ቲዬሪ ሆንሪ፤ ሮቢ ኪን፤ ለንደን ዶናቫንና ዴቪድ ቤካም ዓይነት ተጨዋቾች ዝውውርን ሊያሳይ ይችላል፡፡ለዝውውር ገበያው መቀዛቀዝ ሰበብ ይሆናሉ ከተባሉ ምክንያቶች ዋንኛው ክለቦች በአውሮፓ ደረጃ ለሚደረጉ ውድድሮች መጠቀም የማይችሏቸውን ተጨዋቾች ለመግዛት ያላቸው ፍላጎት ያነሰ በመሆኑ ነው፡፡በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግና በዩሮፓ ሊግ ተወዳዳሪ የሆኑ ክለቦች እርስ በራስ የዝውውር ግብይት መግባታቸው የማይጠበቅ ይሆናል፡፡ በአህጉራዊ ውድድሮች ተሳታፊ ያልሆኑ ክለቦችም ቢሆኑ እንኳን በየሊግ ውድድሮቻቸው ከባድ ፉክክር ውስጥ ስላሉ ተጨዋቾችን ለመሸጥ ፍላጎት ስለማይኖራቸው ለገበያው መቀዝቀዝ ተጨማሪ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ይገለፃል፡፡በአዲስ አመት የዝውውር ገበያ የሚገዙ ተጨዋቾች ውጤታማነትን አጠራጣሪ የሚያደርጉ መረጃዎች ደግሞ ባለፈው አመት ቼልሲ የገዛውን ፈረንናንዶ ቶሬስና ሊቨርፑልን የተቀላቀለውን አንዲ ካሮልን እንዳልተሳካላቸው በምሳሌነት ይጠቅሳሉ፡፡በውድድር ዘመኑ መግቢያ ላይ የእንግሊዙ ፕሪሚዬር ሊግ የተጨዋቾች ዝውውር ወጪ ከባለፉት አመታት በ60በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ለበርካታ የአውሮፓ ሊጎች ተጠቃሚነት ምክንያት ነበር፡፡ በ2011 በአጠቃላይ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ክለቦች በዝውውር ገበያ 700 ሚሊዮን ፓወንድ ሲያወጡ በጣሊያን ሴሪኤ 400 ሚሊዮን ፓውንድ፤ በስፔን ላሊጋ 300 ሚሊዮን ፓውንድ እንዲሁም በፈረንሳይ ሊግ 1 ክለቦች 165 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ ተደርጓል፡፡ይሄን የመሰለ የግብይት ሁኔታ ነገ ከሚከፈተው የ2012 የአዲስ አመት የዝውውር ገበያና ከዚያም በሃላ በሚቀጥሉት የውድድር ዘመናት ተመልሶ እንደማይመጣ ባለሙያዎች እየተነበዩ ናቸው፡፡ ዋና ምክንያቱም በአውሮፓ አገራት መጠነ ሰፊ የኢኮኖሚ ቀውስ ጋር በተያያዘና የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ከ2013 ጀምሮ ተግባራዊ አደርገዋለሁ በሚለው የፋይናንስ ጨዋነት አስገዳጅ ደንብ ጋር ክለቦች ላለመጋጨት በሚከተሉት አቅጣጫ መሆኑንም ይገልፃሉ፡፡በዚሁ የተቀዛቀዘ የዝውውር ገበያ የሁለቱ የስፔን ክለቦች ሪያል ማድሪድና ባርሴሎና ሚና መደብዘዙ ሲስተዋል፤ በጣሊያን ኤሲ ሚላን የማን ሲቲውን ቴቬዝ ለመውሰድ ያለው ፍላጎት፤ በእንግሊዝ ማንችስተር ዩናይትድ የኢንተር ሚላኑን ዌስሊ ስናይደር መመኘቱ፤ አርሰናል ለጀርመኑ ፖዶልሰኪ ዝውውር ማነጣጠሩ ዋና ዋናዎቹ ወሬዎች ናቸው፡፡

 

 

Read 3502 times Last modified on Saturday, 31 December 2011 11:43