Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 31 December 2011 11:49

ዊል ስሚዝ ከ4 ዓመት በኋላ ወደ ትወና ተመለሰ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ለአራት ዓመት ከፊልም ሥራ ርቆ የቆየው የ43 ዓመቱ ዝነኛው የፊልም ተዋናይ ዊል ስሚዝ በአዲስ ፊልም ወደትወና እንደተመለሰ ተገለፀ፡፡ዊል ስሚዝ ከቶሚሊ ጆንስ ጋር የሚተውንበት አዲስ ፊልም የ”ሜን ኢን ብላክ” ተከታታይ ፊልም 3ኛ ክፍል እንደሆነ ታውቋል፡፡ በሚተውንባቸው ፊልሞች ከፍተኛ ገቢ በማስገባት የሚታወቀው ተዋናዩ፤ ከሳምንት በፊት መሞቱን የሚገልፁ ዘገባዎች ተሰራጭተው የነበረ ሲሆን መረጃው ሐሰተኛ እንደሆነና ወደትወና እንደተመለሰ “ቲ ኤም ዜድ” አመልክቷል፡፡ የፊልሙ ሁለተኛ ክፍል ለዕይታ ከበቃ ከ12 ዓመት በኋላ የተሠራው “ሜን ኢን ብላክ 3” 215 ሚሊዮን ዶላር በጀት እንደተመደበለት ለማወቅ ተችሏል፡፡ የ”ሜን ኢን ብላክ 3”  ፊልም ቀረፃ ከጥቂት ወራት በፊት መጠናቀቁን የሚያመለክቱ መረጃዎች፤ ከአራት ወራት በኋላ ለእይታ የሚበቃ ሲሆን በፊልሙ ላይ ዊል ስሚዝ ከቶሚሊ ጆንስ ጋር ከሌላ ዓለም የመጡ ፍጡራንን ውጊያ ሲገጥሙ ያሳያል፡፡ በ1997 እ.ኤ.አ ለእይታ የበቃው የ”ሜን ኢን ብላክ” የመጀመርያ ክፍል 251 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያስገኘ ሲሆን በ2002 የተሰራው “ሜን ኢን ብላክ 2” ደግሞ ከ190 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት ችሏል፡፡

 

 

 

Read 1762 times Last modified on Saturday, 31 December 2011 11:53