Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 31 December 2011 11:55

ሚል ጊብሰን በፍች ለኪሳራ ተዳርጓል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ለቀድሞ ሚስቱ 425 ሚ. ዶላር እንዲያካፍል ተበይኖበታል

የሆሊዉዱ ዝነኛ የፊልም ባለሙያው ሜል ጊብሰን በተደጋጋሚ በገጠመው የጋብቻ ፍቺ ለከፍተኛ ኪሳራ እየተዳረገ እንደሆነ ተገለፀ፡፡ ለ31 ዓመት ያህል በትዳር አብራው የዘለቀችው የቀድሞ ሚስቱ ሮቢን ዴነስ በጠብ እንደተለየችው የሚታወቅ ሲሆን ከሁለት ዓመት በፊት ፍ/ቤት የሃብት ክፍፍል እንዲወስንላት በጠየቀችው መሰረት ሰሞኑን ጊብሰን ካለው የ850 ሚ.ዶላር ሃብት ላይ 425ሚ ዶላር እንድትካፈል ተፈርዶላታል፡፡ የ55 ዓመቷ ሮቢን ዴነስ የተካፈለችው የሃብት መጠን በሆሊዉድ ታሪክ በከፍተኛነቱ ሪከርድ እንደያዘ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ከ20 ዓመት በፊት ደግሞ በፍቺ ለተለያያት ሚስቱ ከሃብቱ ላይ 100 ሚሊዮን ዶላር ያካፈለው ስቲቨን ስፒልበርግ፤ ከሜል ጊብሰን ቀጥሎ ከፍተኛውን ገንዘብ የከፈለ የሆሊውድ ሰው ሆኗል፡፡ የሜል ጊብሰንን ለየት የሚያደርገው ከስድስት ወር በፊት ኦክሳና ግሪግሮቫ ከተባለች ፍቅረኛው ጋር በፀብ ተለያይቶ በፍ/ቤት በተወሰነበት መሰረት ተጨማሪ 750ሺ ዶላር መክፈሉ ነው፡፡ ሜል ጊብሰን በተዋናይነት፤ በፕሮዱዩሰርነትና በዲያሬክተርነት በሰራባቸው ከ30 በላይ ፊልሞች በአጠቃላይ ከ4.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አስገኝቷል፡፡

 

 

Read 3311 times Last modified on Saturday, 31 December 2011 11:58