Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 31 December 2011 12:10

“የሕይወት ጉዞዬ እና ትዝታዎቼ” ሊመረቅ ነው “ቅርጫት ያጡ ፍሬዎች” ለንባብ በቃ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በተለያዩ የሕትመት ውጤቶች በተለይ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ በሚያወጣቸው መጣጥፎቹ የሚታወቀው አበባየሁ ለገሠ “ቅርጫት ያጡ ፍሬዎች”  በሚል ርእስ አዲስ የግጥም መጽሐፍ ለንበብ አበቃ፡፡ 89 አጫጭር እና ረዣዥም ግጥሞችን ያካተተው ባለ 100 ገፅ መፅሐፍ ዋጋ በሃገር ውስጥ 25 ብር ሲሆን በውጭ ሀገራት ደግሞ 15 ዶላር ነው፡፡ በሌላም በኩል የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር አባል የሆኑት ዶ/ር ጌታቸው ተድላ በህይወት ታሪካቸው ዙሪያ ያሳተሙት “የሕይወት ጉዞዬና ትዝታዎቼ” የተሰኘ መፅሐፍ ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት በጣሊያን የባህል ተቋም ይመረቃል፡፡ በመፅሐፉ ምርቃት ላይ የኪነጥበብ ባለሙያዎችና ወዳጆች እንዲገኙ ተጋብዘዋል፡፡ አቢሲኒያ የስነ ጥበብና የሞዴሊንግ ማሰልጠኛ ተቋም ለአንድ አመት በሥዕልና በቅርፃ ቅርፅ፣ በቴአትርና በሙዚቃ ትምህርት ለ10 ወራት ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ነገ ጠዋት ከ3፡30 ጀምሮ በሃገር ፍቅር ቲያትር የሚያስመርቅ ሲሆን፤ የተመራቂ ተማሪዎች ሥራዎች የሚታዩበት ኤግዚቢሽን ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት በብሔራዊ ቴአትር የሚከፈት ሲሆን ኤግዚቢሽኑ ለ10 ቀናት ለህዝብ ክፍት ሆኖ ይቆያል ተብሏል፡፡

 

 

Read 1953 times Last modified on Saturday, 31 December 2011 12:11