Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 31 December 2011 12:12

“ቀዮ” እና “ሳመኝ” ፊልሞች ዛሬና ነገ ይመረቃሉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በዘራፍ ፊልም ፕሮዳክሽን የተዘጋጀው “ቀዮ” የፍቅር ኮሜዲ ፊልም ዛሬ በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተሞች ይመረቃል፡፡ ዋነኛ የምርቃት ሥነ ሥርአቱን በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ትያትርና ባህል አዳራሽ ያደረገውን “ቀዮ”ን የፃፈው ኤልያስ ሙላለም ሲሆን አዘጋጁ ቢኒያም ዮሐንስ ነው፡፡ የ100 ደቂቃ ፊልሙን ለማዘጋጀት አምስት ወር የፈጀ ሲሆን ሜላት ነቢዩ፣ ኤቪያን አማኑዔል፣ ዘነቡ ገሠሠ፣ ቅድስት አስመላሽና ሌሎች ተውነውበታል፡፡ በሌላም በኩል “በዋን ፕላኔት” ፊልም ፕሮዳክሽን የተዘጋጀው “ሳመኝ” ልብ አንጠልጣይ ፊልም በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ነገ የሚመረቅ ሲሆን ጥር 7/2004 ዓ.ም ደግሞ በልዩ ፕሮግራም በብሔራዊ ትያትር እንደሚመረቅ ታውቋል፡፡ የፊልም ስክሪፕቱን ኪሩቤል ሳሙኤል የፃፈው ሲሆን ዮሐንስ ዳምጤ አዘጋጅቶታል፡፡ የ105 ደቂቃ ፊልሙ በዘጠኝ ወራት የተሰራ ሲሆን የሺ ደምበላሽ፣ አለባቸው መኮንን፣ ሰገን ይፍጠር እና ሌሎች ተውነውበታል፡፡

 

 

Read 3608 times Last modified on Saturday, 31 December 2011 12:15