Friday, 06 January 2012 08:22

የኢ.እ.ፌ ፕሬዝዳንት ሹመቶች አገኙ

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

ከወራት በፊት በተካሄደው 61ኛው የፊፋ ኮንግረስ ላይ የፊፋን ቋሚ ኮሚቴ እንደገና ለማቋቋም በተላለፈው ውሳኔ በተያያዘ እያንዳንዱ አባል ሀገርተወካይ እንዲኖረው  ኮንግረሱ ያሳለፈውን ውሳኔ ወደ ተግባር ሲሸጋገር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ሳህሉ ገ/ወልድ የፊፋ ስትራቴጂክ ኮሚቴ አባል ሆነው መመረጣቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኮሚዪኒኬሽን ክፍል አስታወቀ፡፡

አቶ ሳህሉ ገ/ወልድ በቅርቡ ታንዛኒያ ላይ በተካሔደው በ35 የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ውድድር ወቅት የሴካፋ አባል ሀገራት ባካሔዱት የጠቅላላ ጉባዔ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው ይታወሣል፡፡በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰራር በማርኬቲንግና ኮሚዩኒኬሽንና መስኮች ለውጦች መታየታቸውን የጠቆመው የፌዴሬሽኑ መግለጫ በቀጣዮቹ ጊዜያቶች የእግር ኳሱን መሰረት በማስተካከልና ከታች ጀምሮ ተኮትኩቶ የሚመጣ የታዳጊ ወጣቶችእግር ኳስንለማስፋፋት ጥረት እንደሚደረግ ገልጿል፡፡ ለብሔራዊ ቡድናችን የጀርባ አጥንት የሆኑትን የክለቦችን የማስፈፀም አቅም ለማሳደግ በእግር ኳስ ፌደሬሽኑ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች አበረታች መሆናቸውን የሚገልፀው መግለጫው በፊፋና በአፍሪካ ተወካዮች ይሄው ጥረት መረጋገጡንም ገልጿል፡፡ አቶ ሳህሉ ገ/ወልድ ሀገራችንም በ2013 እኤአ የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ(ሴካፋ) የክለቦች ሻምፒዮና እንድታዘጋጅ በማስቻል ጉልህ ሚና ተጫውተዋል፡፡

 

Read 2858 times Last modified on Friday, 06 January 2012 08:26