Monday, 20 October 2014 08:28

“የምሽት እንግዳ” መፅሀፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

   በአስራት ከበደ ተደርሶ የተዘጋጀውና “የምሽት እንግዳ” የሚል ርዕስ የተሰጠው ልብወለድ መፅሀፍ ሰሞኑን ገበያ ላይ ውሏል፡፡ አፅመ ታሪኩ ከምድር ባቡር ሃዲድ ጋር የተቆራኘው ይሄው መፅሀፍ፤ ታሪኩ ከይፋት ተነስቶ ወደ ፈረንሳይ ትልልቅ ከተሞች የሚዘልቅና በአንድ ምዕተ ዓመት የጊዜ ክልል ውስጥ የሚያጠነጥን እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የታሪኩ አጓጊነትና ሲኒማዊ አገላለፅ ቀጣዩን ሂደት በጉጉት ለመከታተል ያስገድዳል የተባለው “የምሽት እንግዳ”፤ በፋርኢስት ትሬዲንግ ታትሞ በ70 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በ314 ገፆች የተቀነበበ ነው፡፡

Read 1556 times