ሩስያዊቷ ሰዓሊ ሥራዎቿን ታቀርባለችየገናን ትውፊት እና ባህል የጠበቀ “አሴና በል” ኪነጥበባዊ ዝግጅት የፊታችን ሰኞ ማምሻውን በብሄራዊ ትያትር ይቀርባል፡፡ ዝግጅቱን ያሰናዳው “ሰርፀ” የሕትመትና ማስታወቂያ ድርጅት ነው፡፡ በእለቱ የገና ጨዋታን ጨምሮ ባህላዊ ዘፈኖች፣ ባለ አንድ ገቢር ተውኔት እና ሌሎች ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች በነፃ ለሕዝብ እንደሚቀርቡ ድርጅቱ አስታውቋል፡፡ ዝግጅቱን የሚያደምቁት “ወይን” ኢትዮጵያ የባህል ቡድን እና “ሉሲ” የባህል ቡድን በመጣመር ነው፡፡በሌላ በኩል የሩሲያዊቷ ሰዓሊ ሌና ፖሎቦክ የስዕል ሥራዎች አርብ ምሽት ፒያሳ በሚገኘው ፑሽኪን አዳራሽ ቀረበ፡፡ “My Sky Motives” በሚል ርእስ የቀረቡት ስዕሎች የኢትዮጵያና የሩስያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት በአንድ ቀን የሚያከብሩትን የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ የተሰናዳ ነው፡፡