Saturday, 22 November 2014 12:30

“ወደ ሀገር ቤት” ፊልም ዛሬ ይመረቃል

Written by  ማህሌት ሰለሞን
Rate this item
(3 votes)

በደራሲና ዳሬክተር ሱራፌል ኪዳኔ ተፅፎ የተዘጋጀው “ወደ ሀገር ቤት” ተሰኘው ሮማንስ ኮሜዲ ፊልም በሀርመኒ ሆቴል ዛሬ ይመረቃል፡፡ ፊልሙ የ1 ሰዓት ከ 37 ደቂቃ ርዝማኔ ሲኖረው ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው በሚመጡ ሰራተኞች ላይ ያጠነጥናል ተብሏል፡፡ በአቤል ፊልም ፕሮዳክሽን በቀረበው በዚህ ፊልም ላይ እንግዳ ሰው ሀብቴ (ቴዲ)፣ ካሳሁን ፍሰሀ (ማንዴላ)፣ ማርታ አሰፋ፣ መኮንን ለአከ፣ አስቴር አለማየሁ እና ሌሎችም ተዋንያን እንደተሳተፉበት ታውቋል፡፡

Read 1845 times