Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Friday, 06 January 2012 10:59

የፖለቲካ ጥግ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ዲሞክራሲ ማለት መስማት የምትፈልገውን ከነገሩህ በኋላ አምባገነኖችን የምትመርጥበት ሥርዓት ነው፡፡

አላን ኮሬን

(እንግሊዛዊ ፀሐፊና ተረበኛ)

***

ቢሮክራሲ የዲሞክራሲ እንቅፋት አይደለም፤ አይቀሬ የዲሞክራሲ ማሟያ እንጂ፡፡

ጆሴፍ አሎይስ ሹምፒተር

(ኦስትርያ ተወላጅ አሜሪካዊ ኢኮኖሚስት)

***

የአሜሪካ ዲሞክራሲና የአሜሪካ ኢኮኖሚ ስኬታማ የነበሩት በግለሰባዊነት ወይም በማህበረሰባዊነት ብቻ አይደለም፤ በሁለቱም የሚቃረኑ አዝማሚያዎች መስተጋብር ጭምር እንጂ፡፡

ፍራንሲስ ፉኩያማ

(አሜሪካዊ ኢኮኖሚስትና የታሪክ ምሁር)

***

ኮሙኒዝም የሚለውን ስም የሚመጥን አገር ውስጥ ነፃነት የለም፡፡ ህዝቡ ሥልጣንን መጠቀም ይፈልጋል፡፡ ግን ቢሰጠው ምን ይሰራበታል?

ቭላድሚር ኢሊች ሌኒን

(ሩሲያዊ አብዮታዊ መሪ)

***

“ኤሌክትሮኒክ ዲሞክራሲ” ለተሳትፎ አዲስ በር ሊከፍት ይችላል፡፡ ነገር ግን ለሁሉም ችግር መፍትሄ አይሆንም፡፡ ዲሞክራሲ ያለ ዲሞክራሲያዊ ሂደት የቃላት ጋጋታ ብቻ ነው፡፡

ዳግላስ ሹለር

(አሜሪካዊ ደራሲ)

***

በኮምፒዩተር የታገዘ የመረጃ አገልግሎት በዲሞክራሲያዊ ህብረተሰብ ውስጥ ትክክለኛ ቦታ አለው ከተባለ የህዝብ ቤተመፃህፍት ውስጥ ነው፡፡

ቴዎዶር ሮስዛክ

(አሜሪካዊ ፀሃፊና አርታኢ)

***

በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚመራ መንግስት እስካለን ድረስ ውለታ እንዲደረግላቸው የሚፈልጉ ሰዎች አይጠፉም፡፡

ሐሪሰን ደብሊው. ፎክስ ጄአር

(አሜሪካዊ ደራሲ)

 

 

Read 3280 times Last modified on Friday, 06 January 2012 11:07

Latest from