Saturday, 13 December 2014 10:18

ለኢቦላ ዘማቾች ሰኞ አሸኛኘት ይደረጋል

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(3 votes)

    የኢቦላ ወረርሽኝ ወደተከሰተባቸው የምዕራብአፍሪካ አገራት ለሚሄዱት 210 የበጎ ፈቃድ ዘማቾችየፊታችን ሰኞ በሸራተን አዲስ የአሸኛኘት ሥነስርዓትይደረግላቸዋል፡፡ ወደ ላይቤሪያና ሴኔጋል የሚጓዙትየበጎ ፈቃድ ዘማቾች፤ ስለበሽታው ምንነት፣ራሳቸውን ከበሽታው ስለሚጠብቁበት መንገድናለኢቦላ ዘማቾች ሰኞ አሸኛኘት ይደረጋል
መታሰቢያ ካሳዬ በአዳዲስ አካባቢዎች ላይ እንዴት መስራትእንደሚችሉ ስልጠና እንደተሰጣቸው ታውቋል፡፡
በኢቦላ ላይ የሚደረገውን ዘመቻ ሂደት በበላይነትከሚመራው የአፍሪካ ህብረት ጋር ውል መፈፀሙንናየበጎ ፈቃድ ተጓዦቹ ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅሞች፣የጤናና የህይወት ኢንሹራንስ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ወጪዎቻቸው ሁሉ በአፍሪካ ህብረትእንደሚሸፈንም ታውቋል፡፡ተጓዦቹ ለጉዞ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮችሁሉ ማጠናቀቃቸውንና ከአልባሳቶቻቸው ጀምሮኢትዮጵያዊነታቸውን የሚያንፀባርቁ እንዲሆኑጥረት መደረጉም ተገልጿል፡፡ ተጓዦቹ የፊታችንሰኞ በሸራተን አዲስ ሆቴል ከፍተኛ የመንግስትባለስልጣናትና የአፍሪካ ህብረት የሥራ ኃላፊዎች
በተገኙበት ሽኝት ይደረግላቸዋል፡፡

Read 1169 times