Monday, 05 January 2015 07:33

ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኞች የመኖሪያ አፓርታማ ሊገነባ ነው

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

          የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኞች የመኖሪያ አፓርታማ በአዲስ አበባ ሊያስገነባ ሲሆን በሁለት ብሎክ አራት ባለ 18 ፎቅ የመኖሪያ ህንፃዎቹ የሚገነቡት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 መገናኛ አካባቢ እንደሆነ ታውቋል፡፡
ሚኒስቴር መ/ቤቱ ህንፃዎቹን ለማስገንባት ዓለምአቀፍ ጨረታ ያሰወጣ ሲሆን በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት ደረጃ 1 የህንፃ ተቋራጭ ኩባንያዎች ብቻ እንደሆኑ ተጠቁሟል፡፡ በጨረታውም የውጭ ሀገር ኩባንያዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሰሞኑን በወጣው በዚህ አለማቀፍ ጨረታ ላይ እንደተጠቆመው የጨረታው አሸናፊ ኩባንያዎች የግንባታ ቁሳቁሶችንና የሰው ሃይልን ጨምሮ ሁሉን ነገር ሙሉ ለሙሉ ራሳቸው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

Read 2377 times