Saturday, 10 January 2015 09:52

የመሬት ዋጋ ንረቱ የነፃ ገበያ ስርአቱ የፈጠረው ነው ተባለ

Written by  ማህሌት ሰለሞን
Rate this item
(10 votes)

በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተው የመሬት ሊዝ ዋጋ ንረት የነፃ ገበያው ስርአት ውጤት እንጂ የፖለቲካ ኢኮኖሚው ነፀብራቅ አይደለም ሲሉ የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር አቶ መኩሪያ ሃይሌ ገለፁ፡፡ የመሬት አቅርቦቱ እየጨመረ ሲሄድ ዋጋው እየተስተካከለ ይመጣል ብለዋል - ሚኒስትሩ፡፡
በከተማዋ ለጨረታ የሚወጣው የመሬት ይዞታ መጠን በጣም ብዙ ነው፤ የዋጋ ንረቱ የታየው  ደግሞ የአንድ ቁራሽ መሬት ነው፤ ይሄ የአገሪቱን ኢኮኖሚ አንደምታ አያሳይም ብለዋል አቶ መኩሪያ ኃይሌ፡፡ “በማክሮ ኢኮኖሚ የንግድ ተወዳዳሪነት ወጪ ከትርፍ ጋር ሲደመር ነው የሽያጭ ዋጋ የሚሆነው፤ ያንን ቁራሽ መሬት በተባለው ዋጋ የገዛው ግለሰብ የራሱ የሆነ ማብራሪያ ይኖረዋል፤ ነገር ግን የነፃ ገበያ ስርአት ነው ከማለት ውጪ ሌላ መልስ ሊኖረው አይችልም” ብለዋል፡፡
በቀጣይ አዲስ አበባ መልሳ የምትታደስ ከተማ በመሆኗ ሰፊ መሬት ማቅረብ ትችላለች፤ የክልል ከተሞችም በከፍተኛ ሁኔታ እያደጉ ስለሆነ መሬት በስፋት ማቅረብ እንችላለን፤ መንግሥት የመሬት ዋጋ ንረቱ በዚያው ይቀጥላል ወይም እየጨመረ ይሄዳል የሚል ስጋት የለውም ያሉት ሚኒስትሩ፤ የመሬት አቅርቦታችንን እየጨመርን ስንሄድ ዋጋው እየተስተካከለ ይመጣል ሲሉ አብራርተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባወጣው 11ኛው ሊዝ ጨረታ በካሬ ሜትር እስከ 305ሺ ብር የግዢ ዋጋ መቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡  

Read 2717 times