ሰዎች ለማሰብ ጊዜ፣ ጥረትና ዝግጅት እንደሚያስፈልግ የተገነዘቡ አይመስልም፡፡ ፖለቲከኞች ንግግር በማድረግ ከመጠን በላይ ከመጠመዳቸው የተነሳ ለማሰብ ጊዜ የላቸውም፡
በትራንድ ረስል
(እንግሊዛዊ ፈላስፋና የሂሳብ ሊቅ)
ፖለቲከኞች ከዋሻው መጨረሻ ብርሃን ሲመለከቱ ተጨማሪ ዋሻ እንዲሰራ የሚያዙ ሰዎች ናቸው፡፡
ሰር ጆን ኪዊንተን
(እንግሊዛዊ የባንክ ባለሙያ)
ፖለቲከኞች የትም ቢሆን አንድ ናቸው፡፡ ወንዝ በሌለበትም ስፍራ ድልድይ ለመስራት ቃል ይገባሉ፡፡
ኒኪታ ክሩስቼቭ
(የሶቭየት ከፍተኛ ባለስልጣን)
እውቅና ሊሰጠኝ ያልፈቀደ እሱ ተቃውሞኛል፡፡
ፍራንትዝ ፋኖን
(የማርቲንኩዋን ማህበራዊ ሳይንቲስት፣ ፊዚሺያንና የሥነ አዕምሮ ባለሙያ)
የሚቃወሙኝን አከብራቸዋለሁ፤ ነገር ግን ልታገሳቸው አልችልም፡፡
ቻርለስ ደጐል
(የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት የነበሩ 1890-1970)
ፖለቲከኛ ወላጅ አልባ ሆኖ መወለድና ላጤ ሆኖ መቅረት አለበት፡፡
ሌዲ በርድ ጆንሰን
(የአሜሪካ ቀዳሚ እመቤት)
ፖለቲከኛ፤ ስራውን ላለማጣት ሲል ማናቸውንም ነገሮች ከማድረግ ወደኋላ አይልም - አርበኝነትን ጨምሮ፡፡
ዊሊያም ራንዶልፍ ኸርስት
(የአሜሪካ ጋዜጣ አሳታሚ የነበረ)
ፖለቲከኛ የመንግስት አውቶሞቢል መጠባበቂያ (ትርፍ) ጐማ ነው፡፡
ጆን ናንሴ ጋርነር
(የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበረ 1868-1967)
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ቢሆኑም እንኳ አንዳንዴ እርቃናቸውን መቆም አለባቸው፡፡
ቦብ ዳይላን
(አሜሪካዊ ዘፋኝ)