Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 14 January 2012 11:14

ፓሪስ ሂልተን ሙዚቃና ቢዝነስን በማጣመር ተሳክቶላታል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በአሜሪካ ሙዚቃና ቢዝነስን አጣምራ በመስራት ስኬት ያስመዘገበችው ፓሪስ ሂልተን፤  ባለፉት ስድስት አመታት በመራቻቸው የንግድ ስራዎች 1.3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማካበቷን “ኮንታክት ሚውዚክ” ዘገበ፡፡ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በርካታ የሙዚቃ ስልቶችን ያካተተ የዘፈን አልበም ለማሳተም ፍላጎት እንዳላት የገለፀችው ፓሪስ ሂልተን፤ በመላው ዓለም በተመረጡ የባህር ዳርቻዎች በስሟ የሚጠሩ መዝናኛዎችን የመክፈት እቅድ እንዳላትም አሳውቃለች፡፡

አርቲስት በስሟ 35 የፋሽንና የኮስሞቲክ ምርት መሸጫ ሱቆቿ ያሏት ሲሆን ከ12 በላይ የፋሽን ምርቶችና ከ14 ዓይነት በላይ ሽቶዎችን በመነገድ ገበያው እንደደራላት ተዘግቧል፡፡ በሪያሊቲ ቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልሞች በመሳተፍ፤ በትላልቅ ፊልሞች በተጋባዥ ተዋናይነት በመስራት በስሟ በምታንቀሳቅሳቸው የፋሽንና የኮስሞቲክስ አምራችና አቅራቢ ኩባንያዎቿ  ስኬታማ እንደሆነች የገለፀው “ኮንታክት ሚውዚክ”፤ ዘንድሮ የአባቷ የነበሩ ዓለም አቀፍ የሂልተን ሆቴሎችን ህጋዊ ወራሽነት መብት እንዳገኘች አመልክቷል፡፡

 

 

 

Read 1882 times Last modified on Saturday, 14 January 2012 11:16