Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 14 January 2012 11:54

የግጥም ጥግ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

መሠረተ ነገር

አንድ ሲባል ብቻ

ሚሊዮን ይቆጠራል

ነጥብ ተደራርቦ

ድልድይ ሆኖ ያስኬዳል

የጠጠር መነሻ

ፒራሚድን ሰርቷል

ጠብታም ንጉስ ነው

አባይን ፈጥሮታል

ያንተ ሥራ

 

 

ላባዬን ያሰርከው

ክንፌን የገጠምከው

ሁሉን አዋቂ አንተ

የጠቢባን አውራ

እኔ ምን አውቃለሁ

ያንተ ዕውር አሞራ

ቀለቤን አሳየኝ

ሳታጋጭ ተራራ

አራርቆ መውለድ

መወለድ ፈልጌ

ወደዓለም መውጣት

ወደ ሰው መኖሪያ

ቪዛ ከለከለኝ

የቤተሰብ መምሪያ

 

ከገጣሚ ኢሳያስ ከበደ

(ዴንቨር፤ ኮሎራዶ)

 

 

Read 4119 times Last modified on Saturday, 14 January 2012 11:56